“ ከፈጣሪ ጋር ጨዋታውን እናሸንፋለን ” ቢኒያም አብረሀ
#Ethiopia | የኢትዮጵያ ከ 17ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን አምበል ቢኒያም አብረሀ ቡድኑ ካለፈው ውድድር በተሻለ ቁመና ላይ መሆኑን ተናግሯል።
ከሴካፋ ውድድር በኋላ ብዙ ተጨዋቾች ወደ ሊጉ ማደጋቸውን የገለፀው ቢኒያም “ ከዚህም ብዙ ተምረናል “ ብሏል።
ብሔራዊ ቡድኑ በአሁኑ ሰዓት “ በጥሩ ሁኔታ ላይ ነው ጥሩ ዝግጅት አድርጓል “ ሲል ተናግሯል።
ከዚህ በፊት ኢትዮጵያ ግብፅን ማሸነፏ ተነሳሽነት ይፈጥራለቸው እንደሆነ የተጠየቀው ቢኒያም “ የእነሱን ታሪክ እንድግማለን ብለን እናስባለን “ ብሏል።
ሁሉም ኢትዮጵያዊ ከጎናችን ይቁም ሲል ጥሪ ያቀረበው የቡድኑ አምበል ቢኒያም “ ፀሎት ያድርግልን ከፈጣሪ ጋር እናሸንፋለን “ብሏል።
እንደ ቲክቫህ ስፖርት ዘገባ የቡድኑ አጥቂ ዳዊት ካሳው በበኩሉ “ ዝግጅታችን ጥሩ ነው ፤ ግብፅን ለማሸነፍ ብዙ ዝግጅት አድርገናል ውጤቱን እናያለን “ ሲል ተናግሯል።
“ እንደ ሴካፋ በዚህም ውድድር የተሻለ ነገር እናደርጋለን ብዬ አስባለሁ እናልፋለን ብዬ አስባለሁ “ ዳዊት ካሳው
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
Source: GetuTemesgen









No comments yet.