መንገድ ዘግተው ሲነግዱ በተገኙ 329 አካላት ላይ እርምጃ መወሰዱ ተገለፀ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በመንገዶች ላይ የሚስተዋሉ ህገ-ወጥ ተግባራትን ለመቆጣጠርና የትራፊክ ፍሰቱን ሰላማዊ ለማድረግ በተከናወነ የቁጥጥር ስራ፣ ያለፈቃድ መንገድ ዘግተው በተገኙ ከ300 በላይ ግለሰቦችና ድርጅቶች ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ መወሰዱን የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን ለመናኸሪያ ሬድዮ አስታውቋል፡፡
በከተማዋ የመንገድ አጠቃቀም መመሪያ ቁጥር 11/2012ን በመተላለፍ፣ ህጋዊ መስመር ሳይከተሉ በራሳቸው ፈቃድ የእግረኛና የተሽከርካሪ መንገዶችን ዘግተው የንግድና የኤግዚቢሽን ስራዎችን ሲያከናውኑ በተገኙ 329 ግለሰቦችና ድርጅቶች ላይ ከ10 ሺህ ብር ጀምሮ የገንዘብ ቅጣት እንደተጣለባቸው የባለስልጣኑ የህዝብ ግንኙነትና ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር ገነት ዲባባ ተናግረዋል፡፡
ያለ ምንም ፈቃድ መንገድ ዘግተው አገልግሎት ሲሰጡ የተገኙ ሁለት ባንኮች በድምሩ 252 ሺህ ብር እንዲቀጡ መደረጉን ዳይሬክተሯ ጠቅሰው፤ ማንኛውም አካል መንገድን ለተለያዩ ኩነቶች በጊዜያዊነት ለመጠቀም ሲፈልግ በየቅርንጫፍ ቢሮዎቹ ቀርቦ ፈቃድ ማግኘት እንደሚገባው ገልፀዋል፡፡
ያለፈቃድ በእግረኛ መንገዶች ላይ ንግድ ማካሄድም ሆነ ድንኳን መትከል በመመሪያው መሰረት እንደሚያስቀጣ ዳይሬክተሯ አንስተው፤ ባለስልጣኑ የከተማዋን የትራፊክ ደህንነት ለማረጋገጥ የጀመረውን የቁጥጥር ስራ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አመላክተዋል፡፡
@seledadotio

No comments yet.