የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን አዲስ አበባ ገቡ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | የፈረንሳይ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን አዲስ አበባ ገብተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማሕበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት÷ የፈረንሳይ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ወንድሜ ኢማኑኤል ማክሮን ወደ ኢትዮጵያ እንኳን ደህና መጡ ስል ሁልጊዜም በልዩ ኩራትና ደስታ ነው ብለዋል።

‎በኢትዮጵያ የሚያደርጉት ሦስተኛው ይፋዊ የሥራ ጉብኝትዎ በፈረንሳይና ኢትዮጵያ መካከል ያለውን የጸና ወዳጅነት ጉልህ ማሳያ ነው ሲሉም አመልክተዋል።

‎ወሳኝ እና ፍሬያማ በሆኑ ውይይቶች ላይ ትኩረት በምናደርግበት በዚህ ወቅት አንድ ነገር እርግጥ ነው፤ እርሱም በኢትዮጵያና በፈረንሳይ መካከል ያለው ትስስር ይበልጥ እየጠነከረ ብቻ የሚዘልቅ ነው ብለዋል።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2