የጤና መረጃ፡ የሃንታ ቫይረስ ስርጭት እና የዓለም ጤና ድርጅት ስጋትበአሁኑ ሰዓት “ኤምቪ ሆንድየስ” (MV Hondius) በተሰ…

- Advertisement -
Sidebar AD
የጤና መረጃ፡ የሃንታ ቫይረስ ስርጭት እና የዓለም ጤና ድርጅት ስጋት
በአሁኑ ሰዓት “ኤምቪ ሆንድየስ” (MV Hondius) በተሰኘች የቱሪስት መርከብ ላይ የተከሰተው የሃንታ ቫይረስ ስርጭት ዓለም አቀፍ ትኩረትን ስቧል።
ቫይረሱ በፈረንሳይ፣ ስፔን እና አሜሪካ በሚገኙ ተጓዦች ላይ እየታየ ሲሆን፣ የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) ሁኔታውን በቅርብ እየተከታተለ ይገኛል።
ዋናው ስርጭት የተከሰተው በአትላንቲክ ውቅያኖስ ላይ በነበረችው MV Hondius በተባለች የደች (Dutch) መርከብ ላይ ነው።
ከመግለጫው ጀምሮ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ፈረንሳይ፣ ስፔን፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ጀርመን፣ ስዊዘርላንድ እና አሜሪካ ውስጥ በሚገኙ ሆስፒታሎች ክትትል እየተደረገላቸው ነው።
እስከ አሁን ድረስ በመርከቧ ላይ በነበሩ 3 ሰዎች ላይ የሞት አደጋ ደርሷል።
እስካሁን በኢትዮጵያም ሆነ በጎረቤት አገራት የተመዘገበ ስርጭት የለም። ነገር ግን ቫይረሱ ከአይጥ ወደ ሰው የሚተላለፍ በመሆኑ ጥንቃቄ አስፈላጊ ነው።
ቫይረሱ እንዴት ይተላለፋል?
ይህ ቫይረስ በዋነኝነት የሚተላለፈው በአይጥ ዝርያዎች ሲሆን፦
1. በአይጥ ንክሻ ወይም አይጦች በነኩት ምግብ።
2. የአይጥ ሽንት ወይም ቆሻሻ ያለበትን አቧራ በመተንፈስ።
3. አሁን የተከሰተው “የአንዴስ” (Andes virus) ዝርያ በጣም አልፎ አልፎ ከሰው ወደ ሰው ሊተላለፍ እንደሚችል ባለሙያዎች ያስጠነቅቃሉ።
ምልክቶቹ ምንድን ናቸው?
* ከፍተኛ ትኩሳት እና ብርድ ብርድ ማለት
* ከባድ የጡንቻ እና የራስ ምታት
* የመተንፈስ ችግር (ሳንባ ላይ ውሃ በመቋጠር)
* ማቅለሽለሽ እና ተቅማጥ
ራስዎን እንዴት ይጠብቁ?
* መኖሪያ ቤትዎን እና የስራ አካባቢዎን ከአይጥ ንክኪ ነጻ ያድርጉ።
* ቆሻሻዎችን በአግባቡ ያስወግዱ።
* ምግብዎን በደንብ ሸፍነው ያስቀምጡ።
* አይጥ ያለባቸውን ቦታዎች ሲያጸዱ የአፍና አፍንጫ ማስገጃ (Mask) እና ጓንት ይጠቀሙ።
ቫይረሱ በአሁኑ ሰዓት እንደ ኮቪድ-19 አይነት የጎላ ስርጭት ባይኖረውም፣ የታየባቸው ሰዎች ላይ ግን እስከ 50% የሞት አደጋ ሊያደርስ ስለሚችል ከፍተኛ ጥንቃቄ ያስፈልጋል።
ይህንን መረጃ ለወዳጅ ዘመድዎ በማጋራት የበኩዎን ይወጡ!
Via WHO
@seledadotio
@seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1