በጎዛምን ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ4 ሰዎች ሕይወት አለፈ፤ 24 ሰዎች ቆሰሉ

- Advertisement -
Sidebar AD

#FastMereja I በዛሬው ዕለት በጎዛምን ወረዳ “ሰንተራ ሜዳ” ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከቀኑ 8:00 ሰዓት ላይ በደረሰ ከባድ የትራፊክ አደጋ የአራት ሰዎች ሕይወት ወዲያውኑ ሲያልፍ፣ 24 ሰዎች ደግሞ ከባድና ቀላል ጉዳት ደርሶባቸው ወደ ሕክምና ተቋም መወሰዳቸውን የጎዛምን ወረዳ ፖሊስ አስታወቀ።

እንደ ወረዳው ፖሊስ መረጃ ከሆነ፣ አደጋው የደረሰው በአዲስና ጉሊት ቀበሌ ልዩ ስሙ ጎሽን ተብሎ በሚጠራው ስፍራ የሕዝብ ማመላለሻ አይሱዙ መኪና (ሰሌዳ ቁጥር ቤጉ-01809) እና መንገድ ሥራ ላይ ከነበረ ሲኖትራክ (ሰሌዳ ቁጥር ኢት-12619) ጋር በመጋጨታቸው ነው። በዚህ አሳዛኝ ክስተት ሁለት ወንዶችና ሁለት ሴቶች በድምሩ የአራት ሰዎች ሕይወት ወዲያውኑ ያለፈ ሲሆን፣ የተቀሩት 24 ተጎጂዎች ደግሞ በደብረ ማርቆስ አጠቃላይ ሪፈራልና ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የሕክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ይገኛል።


Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1