#Ethiopia | የዓለም አትሌቲክስ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጆን ሪጅን እና የጨረታዎች፣ ውድድሮችና ሁነቶች ዳይሬክተር ማርክ ኸረስት በኢትዮጵያ የሚያደርጉትን ይፋዊ የሥራ ጉብኝት አከናውነዋል።
ከፍተኛ አመራሮቹ በቆይታቸው ከባህልና ስፖርት ሚኒስቴር፣ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ኃላፊዎች ጋር ፍሬያማ ውይይት አድርገዋል።
በተጨማሪም ግንባታው በመከናወን ላይ የሚገኘውን የአደይ አበባ ስታዲየምን ጨምሮ፣ ለስፖርቱ ዕድገት ወሳኝ የሆኑ የመሠረተ ልማት ግንባታዎችን በአካል ተገኝተው ጎብኝተዋል።
ጉብኝታቸውን አስመልክተው መግለጫ የሰጡት ዋና ሥራ አስፈጻሚው ጆን ሪጅን፤ “ከ25 ዓመታት በፊት ለታላቁ ሩጫ አዲስ አበባ መጥቼ ነበር፤ አሁን ግን ከተማዋ እጅግ ተለውጣለች፣ በሚገርም ሁኔታም ዘምናለች” ብለዋል።
በተመለከቷቸው መሠረተ ልማቶችና ከመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ጋር ባደረጓቸው ውይይቶች እጅግ መደሰታቸውን የገለጹት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፤ “የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ብሩህ ቀን እየመጣ ነው” ሲሉ ያላቸውን ታላቅ ተስፋ ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮናን ጨምሮ ታላላቅ ዓለም አቀፍ ውድድሮችን ለማስተናገድ ያቀረበችው ጥያቄም በጥሩ ሂደት ላይ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ኮማንደር ስለሺ ስህን በበኩላቸው፤ የዓለም አትሌቲክስ ከፍተኛ አመራሮች ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት እያሳዩ ላለው ድጋፍና ማበረታቻ የላቀ ምስጋና አቅርበዋል።
ኢትዮጵያ የ2028 “አልቲሜት” ሻምፒዮንሽፕ እና የ2031 የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ለማስተናገድ ያቀረበችውን ጥያቄ ከግብ ለማድረስ፣ ፌዴሬሽኑ ከዓለም አትሌቲክስ ጋር በቅርበትና በትብብር እየሠራ መሆኑን ፕሬዝዳንቱ አረጋግጠዋል።
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
#ebcsport #Ethiopia #EBC #ኢትዮጵያ #አትሌቲክስ #ፌዴሬሽን
Source: GetuTemesgen









No comments yet.