የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በኢትዮጵያ የነበራቸውን የሥራ ጉብኝት አጠናቀው ተሸኙ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በኢትዮጵያ ሲያደርጉት የነበረውን ይፋዊ የሥራ ጉብኝት በስኬት አጠናቀው ከሀገር መውጣታቸው ታውቋል፡፡

ፕሬዝዳንቱ በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ በነበራቸው ቆይታ የተለያዩ ዲፕሎማሲያዊ ኩነቶችን ካከናወኑ በኋላ አመሻሹን በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ አማካኝነት አሸኛኘት ተደርጎላቸዋል፡፡

የፕሬዝዳንት ማክሮን ጉብኝት በርካታ ውጤታማ ተግባራት የተከናወኑበት ሲሆን ከእነዚህም መካከል ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር በመሆን የሳይንስ ሙዚየምን መጎብኘታቸው እንዲሁም በብሔራዊ ቤተ መንግሥት የተካሄደው የሁለትዮሽ ውይይት ተጠቃሽ ናቸው፡፡

በቆይታቸውም በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር የሚያስችሉ የኃይል እና የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ስምምነቶች ተፈርመዋል፡፡

ከእነዚህም መካከል ለታዳሽ ኃይል እና ለዲጂታላይዜሽን ፕሮግራም የሚውል የ54 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዩሮ የብድር ስምምነት እንዲሁም የ150 ሜጋ ዋት የጂኦተርማል ኃይል ልማት የመንገድ ካርታ ይገኙበታል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ እንደገለጹት በቆይታው የተደረጉት ውይይቶች በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ወዳጅነት እና አጋርነት ይበልጥ ያጠናከሩ ናቸው፡፡

ይህ ጉብኝት በኢትዮጵያ እና በፈረንሳይ መካከል ለሚኖረው የወደፊት የሁለትዮሽ ግንኙነት ጠንካራ መሠረት ጥሎ ማለፉንም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለው ገልጸዋል፡፡

#ኢትዮጵያ #ፈረንሳይ #ዲፕሎማሲ #ኢኮኖሚ #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa



Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2