ቅዱስ ፓትርያርኩ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ውስጥ የሚገነቡ የልማት ሥራዎችን ተዘዋውረው ተመለከቱ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ የኢትዮጵያ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በዋናው ጠቅላይ ቤተክህነት ግቢ ውስጥ በግንባታ ላይ ያሉ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን በቦታው ተገኝተው ጎብኝተዋል።

በዚሁ የሥራ ምልከታ ወቅት በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ላይ በመሳተፍ ላይ የሚገኙ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ቅዱስነታቸውን አጅበዋል።

በጉብኝቱ ላይ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ፣ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ፣ የመንፈሳዊ ዘርፍ ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ ንቡረ ዕድ ኤልያስ አብርሃ፣ የማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዘርፍ ምክትል ሥራ አስኪያጅ ፕሮፌሰር ግርማ ባቱ እንዲሁም የጠቅላይ ጽሕፈት ቤቱ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

በጉብኝቱም በግቢው ውስጥ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ሥራዎች የሚገኙበት ደረጃ ተገምግሟል።

#ቤተክርስቲያን #ልማት #ፓትርያርክ #ኢትዮጵያ #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1