የኮሚሽነር ዘገየ አስፋው የቀብር ሥነ ሥርዓት በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተከናወነ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር የነበሩት የዘገየ አስፋው የሽኝት እና የቀብር ሥነ ሥርዓት በዛሬው ዕለት በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈጽሟል።

በዚሁ የቀብር ሥነ ሥርዓት ላይ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር፣ የከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አመራሮች፣ የሟች ቤተሰቦችና ወዳጅ ዘመዶች በተገኙበት በክብር አርፈዋል።

ኮሚሽነር ዘገየ አስፋው በኢትዮጵያ የታሪክ ሂደት ውስጥ መሬት ለአራሹ እንዲሆን ከታገሉና አዋጁ እንዲጸድቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ካበረከቱ ቀዳሚ ግለሰቦች መካከል አንዱ ነበሩ።

ረጅም ዘመናቸውን በተለያዩ የመንግሥት የኃላፊነት እርከኖች ላይ በመመደብ ሀገራቸውን በታማኝነት ማገልገላቸው በሕይወት ታሪካቸው ላይ ተገልጿል።

ጋዜጠኛ እና ኮሚሽነር ዘገየ አስፋው በሕመም ምክንያት ሕክምና ሲከታተሉ ቆይተው በተወለዱ በ84 ዓመታቸው ግንቦት 3 ቀን 2018 ዓ.ም ማለፋቸው ይታወሳል።

#ሀገራዊምክክር #መሬትለአራሹ #ዘገየአስፋው #ኢትዮጵያ #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1