#FastMereja I የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለ2026ቱ የዓለም ዋንጫ ወደ አሜሪካ ለሚጓዙ ደጋፊዎች ጥለውት የነበረውን የቪዛ ማስያዣ ቅድመ ሁኔታ ማንሳቱን አስታወቀ።
ከዚህ ቀደም በፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ከ50 ሀገራት የሚመጡ መንገደኞች ከ5,000 እስከ 15,000 ዶላር ተመላሽ የሚሆን ገንዘብ እንዲያስይዙ ተደንግጎ የነበረ ቢሆንም፣ አሁን ግን የውድድሩ ተጫዋቾች፣ የስፖርት አመራሮች እና የጨዋታ ትኬት ያላቸው ደጋፊዎች ይህ ክፍያ እንደማይመለከታቸው ተገልጿል።
ይህ ውሳኔ በተለይ ለዓለም ዋንጫው ማለፋቸውን ላረጋገጡና በደንቡ ተጽዕኖ ስር ለነበሩት አምስት የአፍሪካ ሀገራት (አልጄሪያ፣ ኬፕ ቨርዴ፣ አይቮሪ ኮስት፣ ሴኔጋል እና ቱንዚያ) ደጋፊዎች ትልቅ እፎይታን እንደሚፈጥር ተነግሯል። ደጋፊዎቹ ከክፍያው ነጻ ለመሆን የፊፋን የቀዳሚነት የቪዛ አሰጣጥ ሥርዓት መጠቀም እንዳለባቸው ተመልክቷል።
የ2026ቱ የዓለም ዋንጫ በዩናይትድ ስቴትስ፣ በካናዳ እና በሜክሲኮ አስተናጋጅነት እንደሚካሄድ ይታወቃል።
Source: FastMereja









No comments yet.