የአውሮፓ ኅብረት አባሏ ሊቱዌኒያ አፍሪካ እና እስያውያን ሴቶችን ሴተኛ አዳሪ እና የኤችአይቪ ተሸካሚ አድርጎ በሳለው የመማሪያ

- Advertisement -
Sidebar AD

የአውሮፓ ኅብረት አባሏ ሊቱዌኒያ አፍሪካ እና እስያውያን ሴቶችን ሴተኛ አዳሪ እና የኤችአይቪ ተሸካሚ አድርጎ በሳለው የመማሪያ መጽሐፍ ከፍተኛ ተቃውሞ ገጠማት

​#Ethiopia | በሊቱዌኒያ ለሰባተኛ ክፍል ተማሪዎች የተዘጋጀ የጂኦግራፊ መማሪያ መጽሐፍ፤ የአፍሪካ፣ ታይላንድ እና ሊቱዌኒያ ሴቶችን ፎቶግራፍ ዝቅ ከሚያደርጉ ገለጻዎች ጋር እንዲያዛምዱ ተማሪዎችን በመጠየቁ ከፍተኛ ቁጣ ቀስቅሷል።

ከገለጻዎቹ መካከል አንዱ፤ “ኤድስን የምትፈራ እና በቅርቡ ለሥራዋ ብቁ እንደማትሆን የምትሰጋ የ29 ዓመት ሴት” ይላል።

ሌላኛ ደግሞ፤ “በታዋቂ የመዝናኛ ስፍራ በአስተናጋጅነት እና በሴተኛ አዳሪነት ትሠራለች፤ ማኅበረሰቡ እሷን እና ልጆቿን ያገላል” የሚል መግለጫ አለው።

​ወላጆች እነዚህ የተዛቡ አመለካከቶች ዘረኛ እና ጾታዊ አድልዎን የሚያንጸባርቁ ናቸው በማለት ያወገዙት ሲሆን አንዳንድ ተቺዎች መጽሐፉ ከስርጭት እንዲወጣ እየጠየቁ ነው።

​ከመጽሐፉ አዘጋጆች አንዱ “የፈለግነው እውነተኛውን ዓለም ማሳየት ነው” በማለት ይዘቱን ተከላክሏል።

ዘገባው የስፑትኒክ ነው።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1