የ2018 ትምህርት ዘመን 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ተፈታኞች ፈተና የሚለማመዱበት አድራሻ ይፋ ሆኗል።

- Advertisement -
Sidebar AD

ደጋግሞ መለማመድ የእውቀትን እና የክህሎትን ጉድለት ይሞላል፤ በራስ መተማመንን ያሳድጋል ሲል አገልግሎቱ ገልጿል።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የ2018 ትምህርት ዘመን 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናን በበይነ መረብ (CBT) ለመስጠት ዝግጅት እያደረገ ይገኛል።

በዚህም ሁሉም ተፈታኞች በተደለደሉበት ክልል ወይም ከተማ አስተዳደር ትይዩ ባለው ማስፈንጠሪያ በመጠቀም USER Name በሚለው ላይ የፈተና አዳራሽ መግቢያ ካርድ ላይ ያለውን አድሚሽን ቁጥር በማስገባት እና Pass word በሚለው ላይ 1234 በማስገባት መጠቀም እንደሚችሉ አሳውቋል።

ተማሪዎች ፈተናውን ለመለማመድም በዴስክቶፕ ኮምፕዩተር፣ በላፕቶፕ ኮምፕዩተር፣ በታብሌት፣ በስልክና በመሰል የኤልክትሮኒክስ መሣሪያዎች ማንኛውንም ዓይነት ኢንተርኔት አማራጭ በመጠቀም ከግንቦት 07/2018 ዓ/ም ከጥዋቱ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ እስከፈተናው ድረስ መለማመመድ እንደሚችሉም ገልጿል።

ተፈታኞች አዲሚሽን ካርድ ከየትምህርት ቤታቸው ማግኘት እንደሚችሉ የተገልጸ ሲሆን በየጊዜው ተማሪዎች የሚለማመዱባቸውን ፈተናዎች በተከታታይ የምንሰጥ መሆኑንም አገልግሎቱ አብራርቷል።
በመሆኑም መምህራን ፣ የትምህርት ቤት አመራርና ወላጆች ተፈታኝ ተማሪዎች እንዲለማመዱ አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ እንዲያደርጉ በአክብሮት ጥሪ እናቀርባለን።

Minister of Education



Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: