ካቮድ ኮሜርሻል እስከ 40% ቅናሽ ያደረገበትን “እፎይታ ኤክስፖ” በጊዮን ሆቴል በይፋ ከፈተ

- Advertisement -
Sidebar AD

#FastMereja I ካቮድ ኮሜርሻል ሪል ስቴት “ዘመናዊ የንግድ ቦታ፤ ከኪራይ እፎይታ” በሚል መሪ ቃል ያዘጋጀው ልዩ የሽያጭ ኤክስፖ በዛሬው ዕለት በጊዮን ሆቴል በይፋ ተከፍቷል።

ይህ ከዛሬ ግንቦት 8 ጀምሮ እስከ ግንቦት 14 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ለተከታታይ ሰባት ቀናት ለጎብኚዎች ክፍት ሆኖ የሚቆየው ልዩ ኤክስፖ እስከ 40 በመቶ የሚደርስ ከፍተኛ የዋጋ ቅናሽ ይዞ ቀርቧል። በሁሉም የኢኮኖሚ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ነጋዴዎች፣ ሥራ ፈጣሪዎችና ድርጅቶች ምቹ የክፍያና የባለቤትነት አማራጮች የተዘጋጁ ሲሆን፣ ደንበኞች ያለምንም ተጓዳኝ ወጪ በቀጥታ ከአልሚው ድርጅት ጋር በመወያየት የሱቅና የቢሮ ባለቤት መሆን እንደሚችሉ ተገልጿል።

የካቮድ ኮሜርሻል በአራት ዓመታት ውስጥ 20 ግዙፍ የንግድ ማዕከላትን በአዲስ አበባ ለመገንባት ያቀደ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት የ3ቱ ግንባታ ተጀምሮ እየተፋጠነ ይገኛል። 4ኛው ሞል ደግሞ በሰኔ ወር በመሃል መርካቶ ግንባታው በይፋ እንደሚጀመር ተገልጿል። ተቋሙ የዲጂታል ቴክኖሎጂዎችን እና ዘመናዊ አሰራሮችን በመጠቀም የቴክኖሎጂ ሽግግር ለማድረግ እየሰራ ከመሆኑም በላይ፣ ወደ ህዝብ ኩባንያነት ለመለወጥ ሰፊ ቅድመ ዝግጅት እያደረገ እንደሚገኝ ተገልጿል።






Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: