በኢትዮጵያ የደም ግፊት በሽታ ስርጭት በ17 ነጥብ 3 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን ጥናት አመላከተ

- Advertisement -
Sidebar AD

📌ከሦስት ዜጎች መካከል አንዱ የደም ግፊት በሽታ ተጠቂ እንደሚሆን ተገልጿል።

#Ethiopia | መናኸሪያ ሬዲዮ ያነጋገራቸው በየካቲት 12 ሜዲካል ኮሌጅ የውስጥ ደዌ ስፔሻሊስት ዶክተር አምደመስቀል መርሻ እንደገለጹት፤ አብዛኞቹ ታማሚዎች ሕይወታቸውና ጤናቸው ለከፍተኛ አደጋ ከተጋለጠ በኋላ ነው ስለ በሽታው ምንነት የሚረዱት።

በዚህም እ.ኤ.አ በ2014 በዓለም ላይ የደም ግፊት ተጠቂዎች ቁጥር 22 በመቶ የነበረ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት ግን ይህ ቁጥር አሻቅቦ 33 በመቶ መድረሱን ያብራራሉ።

እንዲሁም በዓለም አቀፍ ደረጃ 1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ሕዝብ የደም ግፊት እንዳለበት ባለሙያው ገልጸው፤ ከዚህ ውስጥ 600 ሚሊዮኑ በሽታው እንዳለባቸው እንኳ እንደማያውቁ እና ማወቅ የቻሉት 800 ሚሊዮኑ ብቻ ሲሆኑ፣ ከእነዚህም ውስጥ 160 ሚሊዮኑ ጨርሶ ሕክምና እንዳልጀመሩ አንስተዋል።

በተጨማሪም ሕክምና ከሚጀምሩት 630 ሚሊዮን ሰዎች መካከል በአግባቡና በሥርዓቱ ሕክምናቸውን የሚከታተሉት 320 ሚሊዮኑ ብቻ ናቸው።

አክለውም እንደ ኢትዮጵያ ባሉ የሰሃራ በታች (ሰብ-ሰሃራ) ሀገራት በተደረገ ጥናት የበሽታው መጠን በ17 ነጥብ 3 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን ገልጸው፤ ዜጎች ወደ ጤና ተቋማት ሄደው የመመርመርና ክትትል የማድረግ ልምዳቸው አነስተኛ መሆን ችግሩን ይበልጥ ውስብስብ እያደረገው እንደሆነ አስረድተዋል።

በሽታው በዓለም አቀፍ ደረጃ በየዓመቱ 3 ነጥብ 7 ትሪሊዮን የአሜሪካ ዶላር ወጪ እንደሚያስወጣም ተገልጿል። በሽታው በዚህ ሁኔታ ከቀጠለ የሟቾች ቁጥር 10 ሚሊዮን ሊጠጋ እንደሚችልም ተጠቁሟል።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1