#Ethiopia | አራትና ከዚያ በላይ የሆኑ ወንዶች በአንድ ላይ በሚገናኙበት ጊዜ የስራና የግል ጉዳዮችን ወደ ጎን በመተው፣ ረጅም ሰዓታትን ስለ እግር ኳስ ክለቦች፣ ተጫዋቾችና ስልቶች በመወያየት እንደሚያሳልፉ ጥናቱ አመልክቷል።
የስነ-ልቦና ባለሙያዎች እንደሚሉት ከሆነ፣ ወንዶች ስለ ግል ህይወታቸው ወይም ስለ ስሜታዊ ጉዳዮቻቸው በቀጥታ መነጋገር ሊከብዳቸው ስለሚችል እግር ኳስን እንደ ማህበራዊ ድልድይ እና የጋራ መግባቢያ መድረክ ይጠቀሙበታል።
ይህ በእግር ኳስ ዙሪያ የሚደረግ ውይይት በወንዶች መካከል ያለውን የወንድማማችነትና የቡድን አንድነት ስሜት በከፍተኛ ደረጃ እንደሚያጠናክረውም ተገልጿል።
በተለያዩ ሀገራት ያሉ የወንዶች የአኗኗር ዘይቤ ቢለያይም፣ በስታዲየሞች፣ በካፌዎች ወይም በመኖሪያ ቤቶች በሚደረጉ ስብሰባዎች ላይ የስፖርቱ አጀንዳነት ሁልጊዜም ቀዳሚ ሆኖ መገኘቱን ጥናቱ አረጋግጧል።
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
#channel1tv #የወንዶችስነልቦና #እግርኳስ #ማህበራዊግንኙነት #የካምብሪጅጥናት #እግርኳስእናወንዶች
Source: GetuTemesgen









No comments yet.