የጄቶር ኢትዮጵያ ዘመናዊ የድህረ-ሽያጭ አገልግሎት ማዕከል በይፋ ተመረቀ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​የጄቶር መኪና አቅራቢ የሆነው ጄቶር ኢትዮጵያ በሀገሪቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የተገነባውን ይፋዊ የድህረ-ሽያጭ አገልግሎት ማዕከል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እና ደንበኞች በተገኙበት በድምቀት አስመርቋል።

የጄቶር መኪናዎችን መሸጥ ብቻ ሳይሆን የተሽከርካሪዎችን ደህንነት እና ዘላቂነት ለመጠበቅ የሚያስችል የተሟላ አገልግሎት ይዞ የመጣ መሆኑ ተገልጿል።

ማዕከሉ በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚገኙ የጄቶር ተጠቃሚዎች አስተማማኝ ዋስትና የሚሰጥ እንደሆነ በምረቃው ስነ-ስርዓት ላይ ተነግሯል።

​የጄቶር ኢትዮጵያ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሙስጠፋ በምረቃው ስነ-ስርዓት ላይ በመገኘት ባደረጉት ንግግር ከዚህ በኋላ ደንበኞች በጄቶር መኪና መለዋወጫ እቃዎች መጥፋት ዙሪያ ሊኖራቸው የሚችለውን ስጋት ሙሉ በሙሉ የሚያስቀር አሰራር መዘርጋቱን አረጋግጠዋል።

ኩባንያው ጥራታቸውን የጠበቁ ኦሪጅናል የመለዋወጫ እቃዎችን እና በዘርፉ የሰለጠኑ ፕሮፌሽናል መካኒኮችን ማደራጀቱን የገለጹት አቶ ሙስጠፋ፣ ደንበኞች ተሽከርካሪዎቹን ሙሉ ልበ ሙሉነት እንዲገዙና ኩባንያው ሁልጊዜም ከጎናቸው እንደሚሆን ኃላፊነት በመውሰድ ቃል ገብተዋል።

​በምረቃው መርሃ-ግብር ላይ ማብራሪያ የሰጡት የጄቶር የድህረ-ሽያጭ አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ አርሴናል በበኩላቸው፣ የማዕከሉ መከፈት ከተራ ተቋማዊ ግንባታ ባለፈ በደንበኞች እና በብራንዱ ላይ የተደረገ ስትራቴጂያዊ ኢንቨስትመንት መሆኑን ገልጸዋል።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu #ጌጡ






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: