#Ethiopia | ኳስ እንደ እንደ መሬት ቅርጽ ድቡልቡልነት እንደ በይነመረብ ኢንተርነት የአለምን ህዝብ በማገናኘት የማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጎኑን ከማሳደግ ረገድ ያለው ሚና ቀላል አይደለም።
በኳስ ጨዋታ ግጥሚያ ውስጥ ብዙ ነገር ትመለከታለህ ለአሸናፊነትህ ግስጋሴ ከባድ ትግል ያለው ውጣ ውረድ ቀላል አይደለም። ዋንጫው አንድ ሲሆነ ተፎካካሪው ግን ብዙ ነው።
በአርሰናል ውስጥ ጽናት፣ ትእግስት፣ዝግጅት፣ልፋት ፈተና፣ውጣ ውረድ፣በጥቂት በሰከንዶች ሽርፍራፊ ብዙ ነገር ፣ዋንጫውን ሲያጣ ትመለከታለህ።
ከዚህም የተነሳ የደጋፊውና የተጨዋቹ ስሜት ከፍና ዝቅ ማለት፣ ለዘመናት በየአመቱ ለዋንጫ እየደረሰ በተደጋጋሚ ማጣቱ ግን ሁልግዜም የዋንጫ ማሸነፍ ራእዩን ከፊት ማስቀመጡ መጣሩ እና መልፋቱ ለዛሬ ዋንጫ አድርሶታል። እኛም ከዚህ ተስፋ ባለመቁረጥ በምናደርገው ትግል የወደፊታችንን የማሸነፍ ራእይ በመያዝ ልንጠብቅ ያስፈልጋል።
ታዲያ እነዚህ በደስታ ስሜት የሰከሩ ደግሞም በተቃራኒው ኳስ ነውና ንዴት ያበገናቸው ቢገናኙ ወይም አንዱ በደስታ ስሜት መግልጫውን ሌላውን ቢነካ በተቀራኒው በሚኖረው የጋለ ስሜት በሚፈጠረው ስሜት ምን ታስባላችው?
ብቻ እውነተኛ ደጋፊ ሰላም ነው። ህግ ሁሌም አለ። ደስታን ሲገልጹ ከስሜትና ስሜት ከሚያስከትለው የህግ ተጠያቂነት ወይም ሊደርስብዎ ከሚችል ድንገት ከሚመጣ የስድብ የመሳሰሉ ነገሮች ራስዎን እየጠበቁ ደስታውን ይግለጹ።
ለአርሰናል ደጋፊዎች በሙሉ ደስ ብሎኛል እንኳን ደስ አላችሁ።
የሕግ ባለሙያው ፋንታሁን ደለለው
”በስፖርታዊ ጨዋነት ደስታችንን እንግለጽ!” 🏆❤️
#getu #FootballDiplomacy #SportManShip #ArsenalChampions #LawAndFootball #FantahunDelelew #LegalAwareness #EthiopianFans #እግርኳስናሕግ #ስፖርታዊጨዋነት #አርሰናል #የደጋፊዎችክብር #ጌጡተመስገን #GetuTemesgen
Source: GetuTemesgen









No comments yet.