ቻይና ካሁን በኋላ “ታዳጊ ሀገር” አትበሉኝ አለች

- Advertisement -
Sidebar AD

​#Ethiopia | በዓለም አቀፍ የንግድና የዲፕሎማሲ መድረክ ላይ ለዓመታት የነበረውን ሚዛን ሙሉ በሙሉ የሚቀይር ታላቅ መግለጫ ከቤጂንግ ተሰምቷል።

​ቻይና ከአሁን በኋላ በዓለም አቀፍ ድርድሮች ላይ “ታዳጊ ሀገር” በመሆኗ ብቻ የምታገኛቸውን ልዩ ጥቅማጥቅሞች፣ ተጨማሪ የጊዜ ሰሌዳዎችን እና ቀለል ያሉ የንግድ ግዴታዎችን እንደማትፈልግ በይፋ አስታውቃለች።

​ይህ ውሳኔ ለበርካታ ዓመታት ቻይና በአንድ ላይ ይዛቸው የኖረችውን ሁለት ተቃራኒ ማንነቶች—በአንድ በኩል የዓለማችን ግዙፍ የኢንዱስትሪ ማዕከል የመሆን፣ በሌላ በኩል ደግሞ በህጋዊ ሰነዶች ላይ “ታዳጊ ሀገር” ተብሎ የመመዝገብ ታሪክ—የሚያበቃላት ይመስላል።

​የቻይና ጠቅላይ ሚኒስትር ሊ ኪያንግ እንደገለጹት፣ ሀገሪቱ በዓለም የንግድ ድርጅት (WTO) ድርድሮች ላይ የሚሰጠውን “ልዩና የተለየ መብት” (SDT) በገዛ ፈቃዷ ለመተው ወስናለች።

​ይህ እርምጃ ቀላል የቴክኒክ ፖሊሲ ለውጥ ሳይሆን፣ ምዕራባውያን ቻይና በታዳጊ ሀገር ስም ተሸሽጋ የራሷን ገበያ ትጠብቃለች በማለት ለአሜሪካና ለአውሮፓ ህብረት ለሚያቀርቡባት ትችት ሙሉ በሙሉ ምላሽ የሰጠ ታላቅ ስልት ነው።

​በሌላ በኩል ቻይና ጥቅማጥቅሙን ብትተወውም “የታዳጊ ሀገርነት” ስሟንና ክበቡን ግን በፍፁም የማትለቅ ሲሆን፣ ይህም ከአፍሪካና ከሌሎች በማደግ ላይ ካሉ ሀገራት ጋር ያላትን ወዳጅነት ለማጠናከርና የ“ግሎባል ሳውዝ” (Global South) ህብረት መሪ ሆና ለመቀጠል ያስችላታል።

​የዘርፉ ባለሙያዎች እንደሚናገሩት ቻይና በተግባር ብዙም የማትጠቀምበትን ህጋዊ መብት በመተው፣ በምትኩ እጅግ ግዙፍ የሆነ የዲፕሎማሲና የፖለቲካ የበላይነት መግዛት የቻለችበት እውነተኛ የማስተር ክላስ ስልት ተብሎ ሊጠቀስ የሚችል ታሪካዊ ክስተት ነው።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu
#menahriaFm ​#China #GlobalTrade #WTO #Geopolitics #GlobalSouth #ChinaEconomy #InternationalRelations #Diplomacy


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: