የሩሲያው በሮኬቶቿ የንግድ ማስታወቂያ መለጠፍ ጀመረች

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​በከፍተኛ ወጪ እና በረጅም ጊዜ ዝግጅት የሚከናወኑት የሕዋ ሮኬት መንኮራኩር ሂደቶች፣ አሁን ላይ የቢሊዮን ዶላር የንግድ ማስታወቂያ መድረክ እየሆኑ መጥተዋል። የሩሲያ ብሔራዊ ስፔስ ኤጀንሲ (ሮስኮስሞስ) ገቢውን ለማሳደግና ግዙፍ የሕዋ ወጪዎቹን ለማቅለል፣ በሕዋ ሮኬቶቹ ላይ የንግድ ማስታወቂያዎችን ማሳየት መጀመሩ ተሰምቷል።

​ባለፈው ዓመት በሩሲያ ፓርላማ በፀደቀው አዲስ ረቂቅ ሕግ መሠረት፣ ስፔስ ኤጀንሲው የታዋቂ የንግድ ምልክት አርማዎችን (Logos) እና መፈክሮችን በሮኬቶች ላይ በመለጠፍ ገቢ እንዲሰበስብ ሙሉ ፈቃድ ተሰጥቶታል። ይህንን ተከትሎም ኤጀንሲው የሀገሪቱን ግዙፍ የፋይናንስ ተቋም ፒኤስቢ ባንክ (PSB Bank) እና የታወቀውን የቡና መሸጫ ሰንሰለት ኮፌማኒያን (Kofemanija) ጨምሮ ለበርካታ ሀገራዊ ብራንዶች የመጀመሪያውን የማስታወቂያ ስራ በተግባር አሳይቷል።

​እንደ ኦዲቲ ሴንትራል ዘገባ ከሆነ፣ ማስታወቂያዎቹ በይፋ መታየት ከጀመሩበት ካለፈው ጥር ወር ጀምሮ ኤጀንሲው ከግል ኩባንያዎች በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ሩብል (የሩሲያ ገንዘብ) ገቢ ማጋበስ ችሏል።

​በሕዋ ሮኬት ላይ ማስታወቂያ ማስነገር እንደ ተራ የጎዳና ላይ ቢልቦርድ ቀላል አይደለም።
የማስታወቂያው ዋጋ የሚሰላው ልዩ ቀመርን በመጠቀም ሲሆን፣ የሚከተሉትን ነጥቦች ግምት ውስጥ ያስገባል፡

-​የማስታወቂያው አጠቃላይ ስፋት
-​በሮኬቱ አካል ላይ የሚይዘው የገጽታ መጠን
-​ማስታወቂያው በሮኬቱ ላይ የሚቆይበት ጊዜ

​የሮኬት መንኮራኩር ሂደት በዓለም ዙሪያ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የሳይንስና የቴክኖሎጂ አፍቃሪያን በቀጥታ ስርጭት የሚከታተሉት ታላቅ ክስተት በመሆኑ፣ ለትልልቅ ኩባንያዎች አይነተኛ የገበያ መድረክ ሆኗል።

የሩሲያ መገናኛ ብዙኃን እንደዘገቡት ከሆነ፣ ኤጀንሲው ከዓመቱ መጀመሪያ ጀምሮ ከታዋቂው የባይኮኑር የሕዋ ጣቢያ (Baikonur Cosmodrome) የማስታወቂያ አርማዎችን ያዘሉ አራት ሮኬቶችን በተሳካ ሁኔታ አስወንጭፏል።

​ይህ አካሄድ የሕዋ ምርምር ድርጅቶች ከመንግስት በጀት ጥገኝነት ወጥተው የራሳቸውን ወጪ በራሳቸው የንግድ ፈጠራ ለመሸፈን ለሚያደርጉት ጥረት ትልቅ ማሳያ ተደርጎ ተወስዷል።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu
​#የሕዋምርምር #ሩሲያ #ሮስኮስሞስ #የንግድማስታወቂያ #ቴክኖሎጂ #ሮኬት #ባይኮኑር #ኢኮኖሚ #ሳይንስ


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1