📌የቀድሞዋ የኢፌዴሪ ርዕሰ ብሔር ሳህለወርቅ ዘውዴ በቅርቡ ሕይወታቸው ያለፈውን የረዥም ዘመን ወዳጃቸውን አምባሳደር ቆንጂት ስነጊዮርጊስ የአርባ ቀን መታሰቢያ በማስመልከት ያሰፈሩት መልዕክት
#Ethiopia | እህቴ፣ ከ40 ዓመት በላይ የማውቃት ታማኝ ጓደኛዬ አምባሳደር ቆንጂት ሥነ ጊዮርጊስ ከተለየችን ሳምንታት፣ 40 ቀናት አለፉ።
የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማን ባውለበለበችበት አገር ሕክምናዋን ጨርሳ ወደምትወዳት፣ ዕድሜ ልኳን ወዳገለገለቻት አገርዋ ለመመለስ የነበራት ተስፋ ትልቅ ነበር።
ሁለት ጊዜ ቪየና ሄጄ ብዙ ተጨዋውተናል። ስንለያይ ያለችኝ እርሷን የተሰማት ነገር እንዳለ ያሳያል። ስጠብቃት የነበረው በብዙ ተስፋ ነበር።
ቆንጅቴ፣ዜጎቻችን፣ ሌሎች አፍሪካውያንና የብዙ አገር ዜጎች ..መልዕክት ሲልኩ፣ ሲያለቅሱ፣ አድናቆታቸውን ሲገልጹ..ነው የከረሙት። የሥራ ባልደረቦችሽና አለቃሽ የነበሩ የአገሪቱ መሪዎች ሸኝተውሻል። ቀና ብለሽ የስንቱን ሕይወት እንደነካሽ ባየሽ ነበር!!
በየቀኑ የምንነጋገረውን፣ምክሮችሽን፣ጥላ ከለላነትሽን…ነው ያጣሁት። ከፍተኛ ሃዘን ነው። በአንድ መስመር መልዕክት የማይገለጽ።ዝም ያሰኘኝ።
ሆኖም የአንቺ የተሟላና ዓላማ ያለው ሕይወት ከለቅሶ በላይ የሚከበር ነው። ጥረሽ ግረሽ ነው ው/ጉ የገባሽው። የ 53 ዓመት አገልግሎትሽ ነው በአግባቡ ሊከበር የሚገባው።ሌላ መለክያ ሊኖር አይችልም።
ወንዳች መካከል ብቸኛ ሴት አምባሳደር መሆን ችግር ነበር። አንቺ ስትመጪ በጋራ ታግለናል። አጠናክሮናል። ተነግሮ አያልቅም።
ቆንጅቴ አሁን ከማታውቂው እረፍት ጋር
እንደተለማመድሽ ተስፋ አለኝ። የማውቅሽን ያህል ግን ስትሯሯጪ፣ ስብሰባ ስትመሪ ትታይኛለሽ።
እረፊ፣ ለፍተሻል። አኩርተሽናል። ነፍስሽን በአፀደ ገነት ያኑርልን።
(ኤርምያስ በጋሻው)
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
Source: GetuTemesgen









No comments yet.