በዳውሮ ዞን፦ የአርሰናል ደጋፊዎች የ120 ሺህ ብር ሰንጋ ሲያዘጋጁ፣ የማንችስተር ደጋፊዎች አቤቱታ አቀረቡ!
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል፣ በዳውሮ ዞን ገሳ ጫሬ ከተማ የሚገኙ የአርሰናል ደጋፊዎች ቡድናቸው ከ22 ዓመታት በኋላ የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ ስላነሳ የ120 ሺህ ብር ዋጋ ያለው የዳውሮ ቅልብ ሰንጋ በሬ መግዛታቸው ተሰማ።
ደጋፊዎቹ የእሁዱን ጨዋታ እና የዋንጫ ዝግጅት በታላቅ ድግስ ለማክበር ሰንጋቸውን አዘጋጅተው ቀኑን በጉጉት እየተጠባበቁ ይገኛሉ።
ይሁን እንጂ ይህ ዝግጅት በከተማዋ በሚገኙ የማንችስተር ዩናይትድ ደጋፊዎች ዘንድ ስጋትንና ቅሬታን ፈጥሯል።
ከስፍራው ለአዘጋጅ ክፍላችን አቤቱታቸውን ያቀረቡ የማንችስተር ደጋፊ እንደገለጹት፦” በአንድነት፣ ተከባብረን እና አብረን በልተን ባደግንባት ማህበረሰብ ውስጥ፣ የአርሰናል ደጋፊዎች ይህንን ዝግጅት ለብቻቸው ማድረጋቸው ተገቢ አይደለም፤ ስግብግብነት ነው»* ሲሉ ቅሬታቸውን ሰንዝረዋል።
አክለውም “ በገዛ ሰፈራችን ሰላም አጥተናል፣ እባካችሁ በስፖርታዊ ጨዋነት ገስጹልን» ሲሉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
የእሁዱ የፕሪሚየር ሊግ ማጠቃለያ ጨዋታ በአውሮፓ መድረክ ብቻ ሳይሆን በገሳ ጫሬ ከተማም በጉጉት የሚጠበቅ ትልቅ የስፖርታዊ ፉክክር ድባብ መፍጠሩ የታወቀ ሲሆን፣ ደጋፊዎች ጨዋታውን በሰላማዊ እና በስፖርታዊ ጨዋነት መንፈስ እንዲከታተሉ መልዕክታችን ነው።
እናንተስ ምን ትላላችሁ? አርሰናሎች ሰንጋውን ይበሉታል ወይስ ማንችስተሮች ይጋበዛሉ?#gursha
@Seledadotio

Related Posts
- Advertisement -

No comments yet.