“በጎዳና ላይ ካገኛችሁኝ መጥታችሁ እቀፉኝ” – ፔፕ ጋርድዮላ

- Advertisement -
Sidebar AD

* ጠዋት ተነስቶ ስፖርት መሥራት ቀረ !

#Ethiopia | ለማንቸስተር ሲቲ ስኬታማ የአስር አመታት ጉዞ የጀርባ አጥንት የነበረው ስፓኝያዊው አሰልጣኝ ፔፕ ጋርድዮላ፣ ቡድኑ በኢትሃድ ስታዲየም ከአስቶንቪላ ጋር ካደረገው የውድድር አመቱ የመጨረሻ ጨዋታ በኋላ ደማቅ የሽኝት መርሃ ግብር ተዘካሂዷል።

ጋርድዮላ በስሜት ተውጦ እና እንባ እየተናነቀው “ይህን ያህል ፍቅር ለምን ሰጣችሁኝ?” በማለት ንግግሩን በጀመረበት ወቅት፣ በስታዲየሙ የታደሙት ደጋፊዎች በከፍተኛ ድምፅ ስሙን በመጥራትና የምስጋና መዝሙራትን በመዘመር ንግግሩን በተደጋጋሚ ያቋርጡት ነበር።

በስንብት ፕሮግራሙ ማጠቃለያ ላይም አሰልጣኙ ለክለቡ ደጋፊዎች ባስተላለፈው መልእክት “ወደየቤታችሁ ከመሄዳችሁ በፊት አንድ ነገር እንድናገር ፍቀዱልኝ፤ በቀጣዮቹ አመታት እዚህ ማንቸስተር ውስጥም ሆነ በማንኛውም የአውሮፓ ከተማ መንገድ ላይ ስታገኙኝ መጥታችሁ ሳታቅፉኝ እንዳታልፉ” ሲል የተማጸነ ሲሆን፣ ይህ ልብ የሚነካ መልእክቱ በአለም ዙሪያ በሚገኙ የክለቡ ደጋፊዎች ዘንድ በሰፊው እየተጋራ ይገኛል።

ፔፕ ጋርድዮላ በማንቸስተር ሲቲ ቆይታው ቡድኑን በ593 ጨዋታዎች ላይ መምራት የቻለ ሲሆን፣ የቀድሞውን አሰልጣኝ የሌዊስ ማክዶውልን የ592 ጨዋታዎች ክብረ ወሰን በመስበር በክለቡ ታሪክ ረጅም ጨዋታዎችን በመምራት ቀዳሚው መሆን ችሏል።

በእነዚህ ጨዋታዎች ውስጥም 416 ድሎችን ሲያስመዘግብ፣ 86 ጊዜ አቻ ወጥቶ በ91ዱ ደግሞ ሽንፈትን አስተናግዷል። በአጠቃላይ በአሰልጣኝነት ዘመኑ 20 ዋና ዋና ዋንጫዎችን ለክለቡ ያስገኘ ሲሆን፣ 5 ጊዜም የኢንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ የአመቱ ምርጥ አሰልጣኝ በመሆን መመረጡ ይታወሳል።

via ዮናታን አየለ

#manchestercity #pepguardiola #football #pep #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa





Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: