የምንገነባው የአውሮፕላን ማረፊያ ሕዝባችንን ይበልጥ ያቀራርባል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የምንገነባው እያንዳንዱ አዲስ የአውሮፕላን ማረፊያ የክልሎችን ኢኮኖሚያዊ አቅም ያነቃቃል እንዲሁም ሕዝባችንን ይበልጥ ያቀራርባል አሉ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስላለፉት መልዕክት÷ የኢትዮጵያ አየር መንገድ 24ኛ የሀገር ውስጥ መዳረሻ የሆነውን እና አዲሱን የነገሌ ቦረና ገዳ አውሮፕላን ማረፊያን በይፋ መርቀናል ብለዋል።

አውሮፕላን ማረፊያው እንደ ቦይንግ 737 ማክስ ያሉ ዘመናዊ አውሮፕላኖችን የማስተናገድ አቅም እንዳለው ገልጸዋል።

የአካባቢውን እንዲሁም ድንበር ተሻጋሪ የንግድ ልውውጥን እና ቱሪዝምን የማሳደግ ርዕይን ሰንቆ በሳምንት ሦስት በረራዎችን እንደሚያስተናግድም ጠቁመዋል።

የምንገነባው እያንዳንዱ አዲስ የአውሮፕላን ማረፊያ ርቀትን በማጥበብ ትስስር ይፈጥራል፣ የክልሎችን ኢኮኖሚያዊ አቅም ያነቃቃል፣ እንዲሁም ሕዝባችንን ይበልጥ ያቀራርባል ነው ያሉት።

የአፍሪካ ኩራት የሆነውና 80ኛ ዓመቱን የያዘው አየር መንገዳችን በእርግጥም የአፍሪካ አዲሱ መንፈስ ነው ሲሉ በመልዕክታቸው ገልጸዋል።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2