1). የፍትሐብሄር ይግባኝ ምንድን ነው?
ይግባኝ (Appeal) ማለት አንድ ወገን በስር ፍርድ ቤት በተሰጠ ውሳኔ ወይም ትዕዛዝ ቅር ተሰኝቶ ከፍ ላለ ፍርድ ቤት “ውሳኔው በህግ፣ በማስረጃ ወይም በስነ-ስርዓት ስህተት አለበት” ብሎ እንዲታረም የሚያቀርበው አቤቱታ ነው።በቀላሉ “የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ እንዲመረመር መጠየቅ ነው።”
2). የይግባኝ ስርዓት አላማዎች (Objective of Appeal System)
(1) . የፍርድ ቤት ስህተት ማረም
ዳኛ በህግ ወይም በማስረጃ ስህተት ቢፈጽም ከፍ ያለ ፍርድ ቤት ያርመዋል።
(2). ፍትህን ማረጋገጥ
ተጎጂ ወገን እንዳይጎዳ ነው።
(3). የህግ አንድነት
ፍርድ ቤቶች ተመሳሳይ ህግን በተመሳሳይ መንገድ እንዲተገብሩ ነው።
3). የይግባኝ መርሆች (Principles of Appeal)
(1). የመሰማት መብት (Right to be Heard)
ሰው በተጎዳ ጊዜ እንዲያመለክት መብት አለው።
(2). ሒደቱ ፍትሐዊ እንዲሆን (Procedural Fairness)
“ማንኛውም ውሳኔ ከመሰጠቱ በፊት ፍትሃዊ ሂደት መከተል” ማለት ነው።
(3). “ፍርድ መጨረሻ ሊኖረው ይገባል” (Finality with Review)
“የፍርድ ውሳኔ መጨረሻ ሲኖረው፣ በተወሰነ ህጋዊ መንገድ እንዲመረመር እድል መስጠት” ማለት ነው።“ፍርድ መጨረሻ ሊኖረው ይገባል፤ ግን ስህተት ካለ የመታረም እድልም ሊኖር ይገባል” ማለት ነው።
4). የ60 ቀን የይግባኝ ጊዜ ምን ያህል አስፈላጊ ነው?
በፍትሐብሔር ስነ-ስርዓት ህግ የመደበኛ ፍትሐብሔር ይግባኝ → 60 ቀን።የገጠር ይዞታ → 30 ቀን ነው።
አላማው ጉዳይ እንዳይንጠለጠል የፍርድ መጨረሻነት እንዲጠበቅ ነው።
5).የመዝገብ ግልባጭ ለምን ያስፈልጋል?
የይግባኝ ፍርድ ቤት አዲስ ክስ አይሰማም የስር ፍርድ ቤት መዝገብ ስራ ይመረምራል።
ስለዚህ የስር ፍርድ ቤት መዝገብ ፦
✔ የቃለ-ችሎት
✔ የማስረጃ
✔ የውሳኔ
✔ የትዕዛዝ ሁሉ በትክክል ተሟልቶ መቅረብ አለበት።
6). የይግባኝ ምክንያት በግልፅ መጻፍ ለምን አስፈለገ?
ፍርድ ቤቱ “ምን ነገር እንዲታረም ትፈልጋለህ?” ይላል።ስለዚህ
“ውሳኔው ተሳስቷል” ብቻ አይበቃም።“ፍ/ቤቱ የሰነድ ማስረጃውን አልመዘነም” ✔ “የህግ ትርጓሜ ተሳስቷል” ✔ “የመስማት መብቴ ተነፍጎኛል” የሚል ግልፅ የቅሬታ የይግባኝ አቤቱታ ምክንያት ማቅረብ ያስፈልጋል።
7). የቃለ-መሐላ አስፈላጊነት
ቃለ-መሐላ ማለት “ያቀረብኩት የይግባኝ አቤቱታ እውነት ነው” ብሎ ህጋዊ ማረጋገጫ መስጠት ነው።የቃለ-መሐላ አላማው ሐሰተኛ አቤቱታ ለመከላከል ነው።
8). የቅጂ ብዛት ለምን ያስፈልጋል?
ሁሉም ተከራካሪዎች አቤቱታውን እንዲያውቁ መልስ እንዲሰጡ
ስለዚህ ቅጂ በተከራካሪዎች ቁጥር መሰረት ይቀርባል።
9). የይግባኝ ስርዓት ጥቅሞች
✔ የዳኝነት ስህተት ይታረማል
✔ ፍትህ ይጠናከራል
✔ የህግ አንድነት ይፈጠራል
✔ የዜጎች መብት ይጠበቃል።
10). የይግባኝ ስርዓት ጉዳቶች / ትችቶች
(1). ጉዳይ ሊዘገይ ይችላል
ተደጋጋሚ ይግባኝ ሊባል ይችላል።ይግባኝ ከአለቀ ወደ ሰበር ይሄዳል።
(2). ወጪ ከፍ ሊል ይችላል
የጠበቃ የኮፒ የክፍያ ሊሆን ይችላል።
(3). የስነ-ስርዓት ጥብቅነት
ትንሽ ጉድለት እንኳ አቤቱታ ሊያሰርዝ ይችላል።
11). ተለመደ የፍርድ ቤት አሰራር
በተግባር ፍርድ ቤቶች መጀመሪያ የጊዜ ገደብ ያያሉ ቀጥሎ መዝገብ ግልባጭ ያሟላ እንደሆነ ያያሉ ከዚያ የይግባኝ ነጥቦች ይመረመራሉ።መጨረሻ ውሳኔውን ማጽናት ማሻሻል መሻር ወደ ስር ፍርድ ቤት መመለስ ይችላሉ።
12). ታሪካዊ አመጣጥ
የዓለም ታሪክ የይግባኝ ስርዓት አጀማመር ከRoman law፣French civil law እና English common law የተቀዳ ነው።
13). በኢትዮጵያ መቼ ተጀመረ?
ዘመናዊ የይግባኝ ስርዓት በ1950ዎቹ–1960ዎቹ
በ1960 የፍትሐብሔር ስነ-ስርዓት ህግ በስርዓተ-ህግ ተደነገገ።
14). ተግባራዊ ምሳሌ
ምሳሌ 1
አበበ በገንዘብ ክስ ተሸነፈ።ዳኛው የአበበ ሰነድ አልመዘነም
አበበ በ60 ቀን ውስጥ የመዝገብ ግልባጭ የይግባኝ ምክንያት
አቅርቦ ይግባኝ ይጠይቃል።
ምሳሌ 2
አበበ ከ60 ቀን በኋላ ይግባኝ አቀረበ።ፍርድ ቤቱ የይግባኝ ማቅረቢያ ጊዜው አልፏል (“Time-barred”) ብሎ ሊያሰናብተው ይችላል።
15). ማጠቃለያ
የፍትሐብሄር ይግባኝ ስርዓት የፍትህ መጠበቂያ ነው።የዳኝነት ስህተት ማረሚያ ነው።ነገር ግን ጥብቅ የስነ-ስርዓት መስፈርት አለው።
ስለዚህ “መብት መኖሩ ብቻ አይበቃም፤ በህጉ ስነ-ስርዓት መሰረት መጠቀም ወይም ማቅረብ ያስፈልጋል።”
ጠበቃና የህግ አማካሪ ዮናስ ወልደየስ
Source: GetuTemesgen









No comments yet.