#Ethiopia | የኢትዮጵያ ኒውክሊየር ኃይል ኮሚሽን ጠንካራ ሀገራዊ የኒውክሊየር መሰረተ ልማት ለመገንባት የሚያስችሉ ከፍተኛ ባለሙያዎችን ለማፍራት ለኢትዮጵያውያን ተማሪዎችና ሰልጣኞች በሩሲያ የነጻ ትምህርት ዕድል ማመቻቸቱን አስታውቋል።
ኮሚሽኑ ለ2026/27 የትምህርት ዘመን በሩሲያ በሚገኙ ስመጥር የሳይንስና የምህንድስና ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ መማር የሚፈልጉ ብቁ አመልካቾች እንዲመዘገቡ ጥሪ አቅርቧል።
የሚሰጡ የትምህርት ዘርፎች በኒውክሊየር ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ላይ ያተኮሩ ሲሆን እነዚህን ዘርፎችንም ያካትታል ፡-
– Nuclear Power Engineering and Heat Physics (BSc & MSc)
– Nuclear Physics and Technology (BSc)
– Nuclear Power Plants Design, Operation and Engineering (BSc)
– Heat Power Engineering (BSc)
– Management in Technological Systems (MA)
የመወዳደሪያ መስፈርቶች ?
• ለመጀመሪያ ዲግሪ (BSc) ዕድሜያቸው ከ20 ዓመት ያልበለጠ እና የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ አማካኝ ውጤታቸው 500 እና ከዚያ በላይ የሆነ።
• ለሁለተኛ ዲግሪ (MSc/MA) ዕድሜያቸው ከ30 ዓመት ያልበለጠ እና በሳይንስና ምህንድስና ዘርፍ በከፍተኛ ውጤት የተመረቁ።
ሴት አመልካቾች ለዘርፉ እንዲበረታቱ ኮሚሽኑ ጥሪ አቅርቧል።
መስፈርቱን ምታሟሉ አመልካቾች ከዛሬ ጀምሮ ባሉት 5 የሥራ ቀናት ውስጥ የትምህርት ማስረጃዎቻችሁን እና ደጋፊ ሰነዶቻችሁን በPDF በማዘጋጀት በኮሚሽኑ የኢሜል አድራሻ enecinfo@enec.gov.et መላክ የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል።
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
Source: GetuTemesgen









No comments yet.