የአለም ማራቶን ክብረ ወሰን ባለቤቷ አትሌት ትዕግስት አሰፋ በገንዘብና ጉልበት ያስገነባችው የቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ተመ

- Advertisement -
Sidebar AD

የአለም ማራቶን ክብረ ወሰን ባለቤቷ አትሌት ትዕግስት አሰፋ በገንዘብና ጉልበት ያስገነባችው የቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ተመረቀ

#Ethiopia | በአለም ማራቶን የክብረ ወሰን ባለቤት የሆነችው ስመ ጥር አትሌት ትግስት አሰፋ እና ባለቤቷ አሰልጣኝ እዮብ ኤልያስ ከፍተኛ የገንዘብ ድጋፍና ጉልበት በማውጣት ያሳነጹት የቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ትናንት በታላቅ ስነ ስርዓት ተመርቋል።

ይህ አዲስ የሃይማኖት ህንጻ የተገነባው በሸገር ሀገረ ስብከት ስር በሚገኘው የሱሉልታና መነአቢቹ ክፍለ ከተማ ቤተክነት ክልል ልዩ ስሙ ሚዛን አትሌት መንደር በተባለው አካባቢ ነው።

የምረቃውን ስነ ስርዓት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ እንዲሁም የደቡብ ምዕራብ ሸዋ እና የሸገር አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የሆኑት ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ በጸሎት መርቀው ከፍተዋል።

ብፁዕነታቸው በወቅቱ ባስተላለፉት መልእክት ለቤተክርስቲያኑ ህንጻ መሳካት ሀብትና ጉልበታቸውን በልግስና ላበረከቱት ለአትሌት ትግስት አሰፋና ለአሰልጣኝ እዮብ ኤልያስ የላቀ ምስጋናና ምርቃት ሰጥተዋል።

በእለቱም ለጥንዶቹ ላበረከቱት የላቀ መንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎት እውቅና ለመስጠት በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ አማካኝነት የክብር ካባ የማልበስ ስነ ስርዓት ተከናውኗል።

ይህ አዲስ መንፈሳዊ ተቋም በአካባቢው ለሚኖሩ ምዕመናን ሰፊ መንፈሳዊ አገልግሎት የሚሰጥ ትልቅ ማዕከል እንደሚሆን በምረቃው ወቅት ተገልጿል።

#tigstassefa #marathon #sululta #sheger #orthodox #church #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: