አሜሪካና ኢራን ተስማሙ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | የሆርሙዝ ሰርጥን ዳግም የሚያስከፍተው የአሜሪካና ኢራን የመግባቢያ ሰነድ (MOU) ይፋ ሆነ።

ስምምነቱ በተደራዳሪዎች መካከል ቢደረግም የፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የመጨረሻ ፊርማ እየተጠበቀ ነው።

የአክሲዮስ ዘገባ እንደሚያሳየው ኢራን በ30 ቀናት ውስጥ በውሃ ውስጥ ያጠመደቻቸውን ፈንጂዎች ለማፅዳት ቃል ገብታለች።

የኢራን መንግስት የኑክሌር ጦር መሳሪያ ግንባታውን እንደሚያቆመውም ተነግሯል።

አሜሪካ በበኩሏ ማዕቀቦችን ስለማንሳት የምትወያይበት ሲሆን በተጨማሪም እንዳይንቀሳቀስ የታገደውን የቴህራንን ሀብት ትለቃለች ።

ዋሽንግተንም ሆርሙዝ ሰርጥን እንደ ኢራን ሁሉ ትከፍታለች ይላል የመግባቢያ ሰነዱ።

ዩራኒዬምን እንዴት ማስወገድ ስለሚቻልበት ሁኔታም ውይይት ያደርጋሉ ቴህራንና ዋሽንግተን።

የመንግስታቱ ድርጅት አገራቱ ተኩስ አቁሙን ገቢራዊ እንዲያደርጉም ጥሩውን አቅርቧል።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu
#nbcEthiopia #America #usa
#iran #newDeal


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: