📌የኢትዮጵያ ቮሊቦል ፌዴሬሽን የክለቦችን ቁጥር ለማሳደግና የስፖርቱን ተወዳጅነት ለመመለስ እየሰራ መሆኑን አስታወቀ
#Ethiopia | የኢትዮጵያ ቮሊቦል ፌዴሬሽን በአገሪቱ የቮሊቦል ስፖርት ተወዳጅነትን ለመመለስና የክለቦችን ቁጥር ለማስፋፋት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን የፌዴሬሽኑ ምክትል ፕሬዝዳንት አበዜ ሱሌማን ገለጹ።
ምክትል ፕሬዝዳንቷ ይህንን የገለጹት በአዲስ አበባ እየተካሄደ የሚገኘውን የወንዶች ፕሪሚየር ሊግ የደርባን ሚድሮክ ሲሚንቶ ውድድር ማጠቃለያን አስመልክቶ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ነው።
እንደ እሳቸው ማብራሪያ እንደ አምቦ ባሉ ኬልል ከተሞች እንዲካሄድ የተደረገ ሲሆን፣ የዛሬው የአዲስ አበባው ውድድር የበርካታ ተመልካቾችን ቀልብ መሳብ የቻለና ስፖርቱ የነበረውን ከፍተኛ ተወዳጅነት መልሶ ለማግኘት የተጀመረውን ጥረት የሚያሳይ ነው።
ወይዘሮ አበዜ ከቀድሞው ዘመን የቮሊቦል እንቅስቃሴ ጋር በማነጻጸር ሲያስረዱ፣ በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ “ስሪ ኢን ዋን” (Three in One) በመባል የሚታወቁትና እንደ ሃንድቦል፣ ባስኬትቦል እና ቮሊቦል ያሉ ስፖርቶችን በአንድ ላይ ማስተናገድ የሚችሉ ሜዳዎች መገንባታቸው ለስፖርቱ እድገት ትልቅ እድል መፍጠሩን ጠቁመዋል። ይሁን እንጂ፣ ቀድሞ በነበረው ጊዜ የነበረው ተነሳሽነት፣ ፍላጎትና በስፖርቱ የመወዳደር ስሜት አሁንም በከፍተኛ ደረጃ ሊበረታታ እንደሚገባ አሳስበዋል።
የአሁኑ ዘመን የክለቦች የዝውውር ሂደት ተጫዋቾች ከአንድ ክለብ ወደ ሌላ ክለብ በገንዘብ የሚዘዋወሩበትን የተሻለ አቅም የፈጠረ ቢሆንም፣ በብሔራዊ ደረጃ ግን አሁንም በክለቦች ላይ ብቻ የተመሰረተ አደረጃጀት እንዳለ ጠቅሰዋል። ፌዴሬሽኑ በኢትዮጵያ ደረጃ የነበሩትን ክልላዊና አገር አቀፍ ውድድሮች ይበልጥ በማጠናከር፣ ወደፊት ኢትዮጵያን በአፍሪካ መድረክ ተወዳዳሪ ማድረግ የሚያስችል የቮሊቦል ስፖርት ለመገንባት ማቀዱን አስታውቀዋል።
ስድስት ክለቦች በተሳተፉበት በዘንድሮው ውድድር ወላይታ ድቻ ካደረጋቸው 9 ጨዋታዎች 21 ነጥብ በመሰብሰብ አሸናፊ ሆኖ ዋንጫውን ወስዷል።
ወላይታ ድቻን በመከተል ሙገር እና መቻል ሁለተኛ እና ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀዋል።
የ2018 ዓ.ም ደርባ ሚድሮክ ሲሚንቶ ወንዶች ፕሪሚየር ሊግ አንደኛ ዙር በአምቦና ወላይታ ሶዶ ከተማ መካሄዱ የሚታወስ ሲሆን፣ ሁለተኛ ዙር ውድድር በአዲስ አበባ ከተማ ተካሄዶ ሊጉ ዛሬ ፍጻሜውን አግኝቷል።
በመጨረሻም በስፖርታዊ ጨዋነት ዙሪያ አስተያየታቸውን የሰጡት ምክትል ፕሬዝዳንቷ፣ ስፖርት ከውድድር ባለፈ የወንድማማችነት ፤ የባህሪ ለውጥ ማምጫ መድረክ መሆኑን ገልጸው፤ በሂደቱ የሚታዩ አንዳንድ ክፍተቶችን በአሰልጣኞችና በሚመለከታቸው አካላት አማካኝነት በማረምና በማስተካከል ስፖርታዊ ጨዋነቱን ይበልጥ ለማስቀጠል እንደሚሰራም አረጋግጠዋል።
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu



Source: GetuTemesgen








No comments yet.