#Ethiopia | በህንድ ራጃስታን ግዛት የሚኖሩ አራት የቤተሰብ አባላትን በመግደል የተጠረጠረችው ሱኒታ ቻውድሃሪ የተባለች ሴት በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውላለች።
ተጠርጣሪዋ የቀድሞ የገጠር መንደር አስተዳዳሪ የነበረውን ባለቤቷን፣ ሁለተኛ ሚስቱን፣ አማቷን እና ሌላ የቅርብ ዘመዷን ከሁለት ልጆቿ ጋር በመሆን በስለት ወግታ መግደሏ ተገልጿል።
ወንጀሉን ለመሸሸግ እና እንደ ድንገተኛ አደጋ ለማስመስል አስከሬኖቻቸውን በስፖርት መኪና (SUV) ውስጥ አቃጥላዋለች።
ድርጊቱ ከተፈጸመ በኋላ ሱኒታ በለቅሶ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ በማልቀስ እና ራሷን በመሳት ወንጀሉን ለመደበቅ ብትሞክርም፣ የፎረንሲክ ምርመራው ግድያ መሆኑን አረጋግጧል።
የአጅሜር ፖሊስ አዛዥ እንዳስታወቁት፣ የግድያው መንስኤ በባለቤቷ ሁለተኛ ጋብቻ ምክንያት በተፈጠረ የረጅም ጊዜ የቤተሰብ ግጭት ነው። በአሁኑ ወቅት ተጠርጣሪዋና ልጆቿ በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው ይገኛል።
ምንጭ፦ ሲናር ሃሪያን/ፊደል ፖስት
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
Source: GetuTemesgen









No comments yet.