የጃፓን ህዝብ ዘር በመተካት ረገድ ዳተኝነት አጥቅቶታል ተባለ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | የጃፓን ህዝብ ቁጥር ባለፉት አምስት ዓመታት ውስጥ ብቻ ከ3 ሚሊዮን በላይ እንደቀነሰ የመንግስት ይፋዊ ሪፖርት አመለከተ።

​በሀገሪቱ የስነ-ህዝብ መረጃ መሰረት በ2020 ዓ.ም 126.1 ሚሊዮን የነበረው የህዝብ ቁጥር በ2025 ዓ.ም ወደ 123 ሚሊዮን ዝቅ ብሏል።

​ይህ ታሪካዊ ማሽቆልቆል ጃፓን እ.ኤ.አ ከ1920 ጀምሮ የህዝብ ቆጠራ መመዝገብ ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ ከፍተኛው ሆኖ ተመዝግቧል።

​ሀገሪቱ እ.ኤ.አ በ2008 ዓ.ም 128 ሚሊዮን በመድረስ ከፍተኛውን የህዝብ ቁጥር ያስመዘገበች ቢሆንም፥ አሁን ባለው አካሄድ እስከ 2070 ዓ.ም ድረስ ቁጥሩ ወደ 87 ሚሊዮን ሊወርድ እንደሚችል ተገምቷል።

​የጃፓን መንግስት ወጣቶች ያለገደብ ልጅ እንዲወልዱ የተለያዩ ማበረታቻዎችን ቢያቀርብም፥ የኑሮ ውድነትና የማህበራዊ ህይወት ለውጦች ጥረቱን ፍሬ አልባ አድርገውታል።

​አሁን ላይ በሀገሪቱ ያለው የውልደትና የሞት ምጣኔ እጅግ የተዛባ ሲሆን፥ በአማካይ አንድ ህጻን ሲወለድ በተቃራኒው የሁለት ሰዎች ህልፈት እየተመዘገበ ይገኛል።

​ይህ እያገረሸ የመጣው የህዝብ ቁጥር መመናመን በሀገሪቱ የኢኮኖሚ እድገት ላይ ከፍተኛ እንቅፋት መፍጠሩ ተነግሯል።

​ከዚህም በተጨማሪ የሰራተኛ እጥረት እያስከተለ መሆኑ እና በጤናው ዘርፍ ላይ ከባድ ጫና እየጣለ እንደሚገኝ ብሄራዊ የስቴትስቲክስ ኤጀንሲው አስታውቋል።

​የችግሩን አሳሳቢነት ይበልጥ ማሳያ የሚሆነው ከሀገሪቱ 47 ግዛቶች ውስጥ በሁለቱ ላይ ብቻ መጠነኛ መረጋጋት ሲታይ፥ በቀሪዎቹ 45 ግዛቶች ግን የህዝብ ቁጥር መቀነሱ በከፍተኛ ፍጥነት ቀጥሏል።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu
​#Japan #DemographicCrisis #JapanPopulation #GlobalNews #Economy #PopulationDecline #AsiaNews


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: