ራይድ ትራንስፖርት ተሸለመ

- Advertisement -
Sidebar AD

RIDE በAfrica’s Best Brands Award ላይ Most Admired Ethiopian Brand በመሆን ለከፍተኛ ሽልማት በቅቷል::

በአዲስ አበባ United Nations Economic Commission for Africa (ECA) በተደረገው የሽልማት ስነ-ስርዓት ላይ ድርጅታችን ይህንን ታላቅ ክብርና ሽልማት በማግኘቱ የተሰማን ደስታ እየገለፅን ÷ በመላው የራይድ ቤተሰብ ስም ለማመስገን እንወዳለን::

ድርጅታችን በ2006 ዓ.ም RIDE የተሰኘውን የንግድ ስም እና ምልክት በኢትዮዽያ አዕምሮ ንብረት ጥበቃ በማስመዝገብ በኢትዮዽያ የመጀመርያውን የኤሌክትሮኒክ ታክሲ አገልግሎት ዘርፍ ፈር – ቀዳጅ ሲሆን በአሁን ወቅት በስፋት አገልግሎቱን እያቀረበ ይገኛል:: በተጨማሪም በFood Delivery እና ተዛማች አገልግሎቶች ላይ በመሪነት እያገለገለ ይገኛል::

ይህንን ትልቅ ብራንድ ስንገነባ በነበረው ሂደት ከጎናችን ለነበራችሁ አሽከርካሪዎች ÷ ደንበኞቻችን እና መላው የራይድ ቤተሰቦች በቀጣይም ከኢትዮዽያ አልፎ በአፍሪካ በምናደርገው ጉዞ አብረውን በዘላቂነት እንደሚወዳጁን እንተማመናለን::

ከRIDE ጋር ወደፊት💛!


Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1