የሜድ ስታር የውስጥ ደዌ ስፔሻሊቲ ክሊኒክ አዲስ ያደራጀውን የህክምና ተቋም አስመረቀ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​በኮሪደር ልማት ምክንያት ከነበረበት የውሃ ልማት ፊት ለፊት አካባቢ ተነስቶ የነበረው ሜድ ስታር የውስጥ ደዌ ስፔሻሊቲ ክሊኒክ፣ ስድስተኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን ምክንያት በማድረግ በአዲስ መልክ በዘመናዊ መልክ ያደራጀውን የህክምና ተቋም የክብር እንግዶች በተገኙበት በዛሬው ዕለት በምረቃ ስነ-ስርዓት አስመርቋል።

ተቋሙ በኮሪደር ልማት ምክንያት ቢፈርስም፣ ላለፉት 14 ዓመታት አገልግሎት ሲሰጥበት በነበረው በዚሁ አካባቢ ለታካሚዎች የትራንስፖርት ምቾትን ታሳቢ ባደረገ ስፍራ ላይ በላቀ የህክምና መሳሪያና አደረጃጀት ስራ መጀመሩ ተገልጿል።

​የክሊኒኩ ባለቤትና መስራች የሆኑት የውስጥ ደዌ ስፔሻሊስት ዶክተር ዳዊት አማረ በምረቃው ወቅት እንደተናገሩት፣ ተቋሙ አንድ ታካሚ ሲመጣ ወደተለያየ ቦታ ሳይንከራተት አስፈላጊውን ምርመራና የባለሙያ እገዛ በአንድ ማዕከል እንዲያገኝ ተደርጎ ተደራጅቷል። ዘመኑ ያፈራቸውን የህክምና መገልገያ ማሽኖች፣ የተሟላ ላብራቶሪ እንዲሁም የኢንዶስኮፒ፣ የኮሎኖስኮፒና የነርቭ ምርመራ ማሽኖችን በማካተት የህክምና ጥራቱን ሳይጓደል አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።

በአሁኑ ወቅት ክሊኒኩ የትርፍ ሰዓት ሰራተኞችን ጨምሮ ለ56 የህክምና ባለሙያዎች የስራ ዕድል የፈጠረ ሲሆን፣ በአጠቃላይ ወደ 23 የሚሆኑ ስፔሻሊስት እና ሰብ-ስፔሻሊስት ዶክተሮች በተቋሙ ውስጥ አገልግሎት እየሰጡ መሆናቸው ታውቋል።

📷 ከበደ መክብብ

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu #ጌጡ






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: