ነገ ኢትዮጵያ ትመርጣለችበፓርቲዎች ስም 10 ሺህ 437 ዕጩዎች እንዲሁም 80 የግል ተወዳዳሪዎች  ለመመረጥ ተዘጋጅተዋል42 የፖ…

- Advertisement -
Sidebar AD
ነገ ኢትዮጵያ ትመርጣለች
በፓርቲዎች ስም 10 ሺህ 437 ዕጩዎች እንዲሁም 80 የግል ተወዳዳሪዎች  ለመመረጥ ተዘጋጅተዋል
42 የፖለቲካ ፓርቲዎች በሰኞው ሀገራዊ ምርጫ እንደሚወዳደሩ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቋል
ቦርዱ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ለሚካሄደው ጠቅላላ ምርጫ ሙሉ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን አስታውቋል።
የቦርዱ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ በአጠቃላይ 54 ሚሊዮን 057 ሺህ 871 መራጮች መመዝገባቸውን ጠቅሰው፤ በፓርቲዎች ስም 10 ሺህ 437 ዕጩዎች እንዲሁም 80 የግል ተወዳዳሪዎች ለምርጫ መቅረባቸውን ይፋ አድርገዋል።
ቦርዱ የምርጫ ቁሳቁሶችን ሙሉ በሙሉ ማድረሱን፣ የዜጎችን ግንዛቤ ለማሳደግ በ5 ቋንቋዎች 19 የሕዝብ ክርክሮችን ማደራጀቱንና ከ250 ሺህ በላይ የታዛቢዎች ባጅ ማሰራጨቱን ሰብሳቢዋ ገልፀዋል።
 
ምርጫውን የአፍሪካ ኅብረት፣ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት እና የሀገር ውስጥ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ይታዘባሉ።
 
በምርጫ ቦርድ የግዜ ሠለዳ መሠረት የድምጽ ውጤት ሰኔ 4 ቀን 2018 ዓ.ም ይፋ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2