ያከበረንን አክብረን የመረጠንን ሰርተንለት የምናልፍ ከሆነ ሁላችንም አሸናፊ እንሆናለን” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር

- Advertisement -
Sidebar AD

ያከበረንን አክብረን የመረጠንን ሰርተንለት የምናልፍ ከሆነ ሁላችንም አሸናፊ እንሆናለን” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

#Ethiopia | ግንቦት 24፣ 2018 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በትውልድ ቀያቸው በሻሻ ድምፅ ሰጥተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በወቅቱ ለመገናኛ ብዙኃን እንደገለጹት፤ የኢትዮጵያ ህዝብ ከማለዳ ጀምሮ በመውጣት በሰልፍ ምርጫ እያካሄደ ይገኛል።

ይህም የሚሻውን ለመምረጥ መካሪ እንደማያስፈልገው ማሳያ መሆኑን ተናግረዋል። እኔ ዛሬ የሚያሳስበኝ ከመራጩ በላይ ተመራጩ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ይህ ህዝብ በቁርጠኝነት የሚሻውን ወስኖ በዲሞክራሲያዊ መንገድ ከመረጠ በኋላ የተመረጡት ሰዎች በዚያ ልክ ታምነው እጃቸውና ልባቸው ንጹህ ሆኖ ደከመን ታከተን ሳይሉ ሰርተው የሀገር ታሪክ ለመቀየርና የህዝቡን ውለታ ለመክፈል ዝግጁነታቸው ምን ያክል ነው የሚለው ነው ሲሉ ተናግረዋል”

በምርጫው ሂደት ያሸነፉ በታማኝነት ማገልገል የተሸነፉ ደግሞ ውጤቱን በጸጋ ሊቀበሉ እንደሚገባ አሳስበዋል።

ጋዜጣ-ፕላስ

​#የ7ኛውጠቅላላምርጫ #ምርጫ2018 #ሻሻ #ጠቅላይሚኒስትርዐቢይ #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: