የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በዛሬው ዕለት እየተካሄደ ያለውን ሰባተኛውን ጠቅላላ ምርጫ አስመልክቶ የቦርዱ ሰብሳቢ ወ/ሮ ሜላተወርቅ ኋይሉ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫቸውም በፀጥታ ችግር ምክንያት 143 የሚሆኑ የምርጫ ጣቢያዎች ምርጫ ሊደርግባቸው ዝግጅት ቢያደርጉም ያልተከፈቱ መሆናቸውን ገልጸዋል።
በአማራና በኦሮሚያ አንዳንድ አካባቢዎች ተከፍተው የተዘጉ እንደ ቀርሳ፣ ኩታበር፣ ቢሎኖፖ፣ መኮሳቺና ሌሎች አካባቢዎች የምርጫ ሂደቱ መቋረጡን ጠቁመዋል።
ከዚህ በተጨማሪ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው መራጮች ሰልፍ መሆናቸውን ያነሱት ዋና ሰብሳቢዋ በተለይም በድጅታል ምዝገባ የተመዘገቡ መራጮችን ላይ መዝግየቶች አሉ ብለዋል።
ችግሩን ለመፍታት እና መራጮች በፍጥነት ለማስተናገድ እየተሰራ መሆኑን ገልጸው ለተፈጠረው መጉላላት ይቅርታ ጠይቀዋል።
እንዲሁም በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ዘልመም እና ሰዳል አካባቢዎች የኔትወርክ ችግር በመኖሩ መረጃ ለመለዋወጥ ተግዳሮት መሆኑን ተናግረዋል።
#አሐዱ
Source: Yeneta Tube









No comments yet.