በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት ከ10 በላይ ኦርቶዶክሳውያን ሲገደሉ

- Advertisement -
Sidebar AD

የ101 ዓመት እድሜ ያለው የቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ሙሉ በሙሉ በእሳት ወድሟል።

የመድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ላይም ዘረፋ የተካሄደ ሲሆን ምእመናን ጽላቱን ይዘው ተሰደዋል፤ መኖሪያ ቤታቸውም ተቃጥሏል።

ከግንቦት 23 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት፣ አሰኮ ወረዳ፣ ጠላታ ጨፋ ቀበሌ እና ካራ ኩፍቴና በሚባሉ አካባቢዎች በኦርቶዶክሳውያን ላይ ያነጣጠረ አሰቃቂ ግድያ ተፈጽሟል።

በአሰኮ ወረዳ ጠላታ ጨፋ ቀበሌ ብቻ በታጣቂ ኃይሎች በተፈጸመ ሰብአዊነት በጎደለው ጥቃት ከ10 በላይ ንጹሃን ኦርቶዶክሳውያን ተገድለዋል።

በአካባቢው 101 ዓመታትን ዕድሜ ያስቆጠረው፣ የጠላታ ጨፋ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ሙሉ በሙሉ በእሳት ወውደሙ ተገልጿል።

በተመሳሳይ ጥቃት በካራ ኩፍቴና መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ላይ ጥቃት የተሰነዘረ ሲሆን፣ የቤተክርስቲያኑ ንብረት የሆኑ ቤቶች በመቃጠላቸው ምእመናን የመድኃኔዓለምን ቅዱስ ጽላት ይዘው በእግራቸው ወደሌላ አካባቢ መሸሻቸው ታውቋል።

በዚሁ በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት በሺርካ ወረዳ በሁለት ወጣት ኦርቶዶክሳውያን ላይ ዘግናኝ ግድያ መፈጸሙ ተሰምቷል።

ድርጊቱ የተፈጸመው ሚታና ዋጂ ቀበሌ ሲሆን፣ ታጣቂዎች ግንቦት 23 ቀን 2018 ዓ.ም ወደ ወጣቶቹ መኖሪያ ቤት በመግባት በቁጥጥር ስር እንዳዋሏቸውና በመቀጠልም ወጣቶቹን ወደ ሚታና ጋዶ ቀበሌ በመውሰድ፣ አንደኛውን በስለት አር ደው፣ ሁለተኛውን ደግሞ በጥይት በመምታት በጭካኔ ሕይወታቸውን እንዳጠፉት ተገልጿል።

ሕይወታቸውን ያጡት የእነዚህ ወጣቶች ሥርዓተ ቀብር ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም በጋዶ ማሕደረ ስብሐት ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን፣ ምዕመናንና በቤተሰብ በተገኘበት በአንድ መቃብር ተፈጽሟል።

በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት በአገልጋዮችና ምእመናን ላይ በተደጋጋሚ ጥቃት እንደሚፈጸምበት ማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ለዓመታት መረጃ እያደረሰ ቢሆንም ዛሬም ድረስ ዘላቂ መፍትሔ አልተገኘም።

መረጃው የማህበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ነው። #FastMereja


Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: