የአዲስ አበባ ከተማ የቀድሞ ከንቲባ አምባሳደር ዓሊ አብዶ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ​የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርን በ27ኛ ከ…

- Advertisement -
Sidebar AD
የአዲስ አበባ ከተማ የቀድሞ ከንቲባ አምባሳደር ዓሊ አብዶ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ
​የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርን በ27ኛ ከንቲባነት ከ1990 እስከ 1995 ዓ.ል. የመሩት አምባሳደር ዓሊ አብዶ ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ተሰማ።
​አምባሳደር ዓሊ አብዶ ባደረባቸው ህመም ምክንያት በህክምና ሲረዱ ቆይተው፣ ዛሬ ሌሊት ህይወታቸው ማለፉ ታውቋል። በአርሲ ድሬ ከተማ ከአባታቸው ከአቶ ዓሊ ሱለይማን እና ከእናታቸው ከወ/ሮ አፀደ ወልደማሪያም የተወለዱት አምባሳደር ዓሊ፣ ከትዳር አጋራቸው ጋር በጋራ ያፈሯቸው ሁለት ሴት እና አንድ ወንድ ልጆች አሏቸው።
​አምባሳደር ዓሊ አብዶ በቆዩባቸው የሥራ ዘመናት ሀገራቸውንና ሕዝባቸውን በቅንነት፣ በታማኝነትና በታታሪነት ሲያገለግሉ የነበሩ መሪ እንደነበሩ ተገልጿል።
​የቀብር ሥነ-ሥርዓታቸው በዛሬው ዕለት ከጁምዓ ሶላት በኋላ፣ በዳለቲ አካባቢ በሚገኘው የሙስሊሞች መቃብር ስፍራ፤ ቤተሰቦቻቸው፣ ወዳጅ ዘመዶቻቸውና የመንግስት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ይፈጸማል።
የኔቲዩብ ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው እና ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ መጽናናትን እየተመኘ፤ አላህ (ሱ.ወ) ጀነተል ፊርዶስ ይወፍቃቸው ዘንድ ዱዓ ያደርጋል።
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: