በቲክቶክ ጸያፍ ንግግር ሲያሰራጩ የነበሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

- Advertisement -
Sidebar AD

​#FastMereja I በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባምባሲ ወረዳ በማህበራዊ ሚዲያ (በተለይም በቲክቶክ) ላይ የመንግስት የስራ ኃላፊዎችን የሚያንቋሽሹ፣ የሚሳደቡ እና የማህበረሰቡን ወግና ልማድ የሚፃረሩ ጸያፍ ቃላትን ሲነዙ የነበሩ ግለሰቦች በህግ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን የባምባሲ ወረዳ ፖሊስ ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

​የባምባሲ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት አዛዥ ኮማንደር ሀሩን ሄረላ እንደገለጹት፣ ተጠርጣሪዎቹ የዲጂታል መድረኮችን በመጠቀም የህዝብን ሞራልና የአካባቢውን ሰላም የሚነኩ ተግባራትን ሲፈጽሙ ቆይተዋል። በአሁኑ ወቅት በግለሰቦቹ ላይ ጥብቅ የምርመራ ሂደት እየተከናወነ ሲሆን፣ የምርመራው ውጤት ተጠናቆ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለህብረተሰቡ ይፋ እንደሚደረግ ፖሊስ ተናግሯል።


Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: