የአሜሪካ ጦር ሄሊኮፕተር በሆርሙዝ ሰርጥ ተከሰከሰ።ሁለት የበረራ ባለሙያዎች አለማግኘታቸውን፣ ግን እና ከአደጋው ስፍራ “መውጣታ…

- Advertisement -
Sidebar AD
የአሜሪካ ጦር ሄሊኮፕተር በሆርሙዝ ሰርጥ ተከሰከሰ።
ሁለት የበረራ ባለሙያዎች አለማግኘታቸውን፣ ግን እና ከአደጋው ስፍራ “መውጣታቸውን” ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ገልጸዋል።
ከዚህ ያለፈ ዝርዝር መረጃ ከመስጠት የተቆጠቡት ፕሬዚዳንቱ፣ ከኢራን ጋር የሚደረገው ስምምነት “እየተቃረበ” ነው ሲሉ ተናግረዋል።
የበረራ አደጋው መንስኤ እስካሁን በግልጽ አልታወቀም ተብሏል።
ሄሊኮፕተሩ መከስከሱ የተሰማው ኢራን እስራኤል ላይ የሚሳዔል ጥቃት ከፈፀመች እና፣ እስራኤልም በጦር አውሮፕላን እና ድሮን የታገዘ የአፀፋ እርምጃ መውሰዷ ከተገለፀ በኋላ ነው።
ክስተቱ ይደረጋል ተብሎ የሚጠበቀውን የሰላም ስምምነት አደጋ ላይ የሚጥል ተደርጎ ተወስዷል።
በተመሳሳይ ሄሊኮፕተሩ የተከሰከሰው በሆርሙዝ ሰርጥ መሆኑ የመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት ያስከተለው የሀይል አቅርቦት መስተጓጎል የበለጠ ጫና ውስጥ እንዲገባ የሚያደርግ ነው ተብሏል። 
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2