የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሁለት ሽልማቶችን ተጎናጸፈ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | የኢትዮጵያ አየር መንገድ በካርጎና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ዘርፎች የአፍሪካ ቀዳሚ በመሆን አሸነፈ።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የካርጎና ሎጂስቲክስ አገልግሎት በዱባይ በተካሄደው የ2026 የአቪዬሽን ስኬት ሽልማት ላይ ሁለት ታላላቅ ሽልማቶችን ተሸልሟል።

አየር መንገዱ በዘርፉ ባሳየው የላቀ ብቃት በአፍሪካ ደረጃ የዓመቱ ምርጥ የካርጎ አየር መንገድና የዓመቱ ምርጥ የኤር ካርጎ ፋርማ አገልግሎት በመሆን ተመርጧል።

የመድኃኒትና ሕክምና ግብዓቶች የጭነት አገልግሎት ሽልማቱ፣ አየር መንገዱ ጥንቃቄና ልዩ ቁጥጥር የሚሹ የሕክምና ምርቶችን በዓለም አቀፍ ደረጃ በከፍተኛ ጥራት ለማጓጓዝ ያለውን ተዓማኒነትና ብቃት ያረጋገጠበት ሆኗል ያለው ቻነል ዋን ነው።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: