90 ሺ ብር በ100 ሺ ብር እየተሸጠ ነው!በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የኮንትሮባንድ ንግድ በመስፋፋቱና የጥሬ ገንዘብ እጥረት …

- Advertisement -
Sidebar AD
📈90 ሺ ብር በ100 ሺ ብር እየተሸጠ ነው!
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የኮንትሮባንድ ንግድ በመስፋፋቱና የጥሬ ገንዘብ እጥረት በማጋጠሙ እጃቸው ላይ ገንዘብ ያላቸው አትርፈው መሸጥ ጀምረዋል ተባለ፡፡
እንደማሳያም 90,000 ብር በ100,000 ብር ይሸጣል፡፡ ከባንኮች አንድ ሰው በቀን ከ500 ብር በላይ ማውጣት አይችሉም መባሉን ሸገር ኤፍ ኤም ዘግቧል፡፡
የህዝብ እንደራሴዎች ም/ቤት አባል እና የቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ የፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊ መብራቱ አለሙ የጥሬ ገንዘብ እጥረት በባንኮች መፈጠሩን እና የኮንትሮባንድ ንግድ መስፋፋትን የተመለከቱት በምርጫ አካባቢያቸው በመተከል ዞን በመገኘት ባደረጉት ህዝባዊ ውይይት መሆኑን ነገረውኛል ብሏል ሸገር፡፡
የኑሮ ውድነቱ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ተባብሷል የሚሉት የህዝብ እንደራሴው ይህንንም በህዝባዊ ውይይታችን ተመልክተናል ብለዋል፡፡

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: