ለጎል አስቆጣሪው ቆሎና ለውዝ የሸለመው ታዳጊ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | የምሽቱ የዎላይታ ዲቻና የቅዱስ ጊዮርጊስ ጨዋታው ከተጠናቀቀ በኋላ ጎል ያስቆጠረውን አብነት ደምሴን ለብቻው ፎቶ ለማንሳት ዳኞች ሜዳውን ለቀው እስኪወጡ በምንጠብቅበት ሰዓት ከጀርባዬ አንድ ለውዝና ቆሎ የሚሸጥ ልጅ አብነትን ሲጠራው ሰማሁትና ስዞር ጎል ስላስቆጠረ ከሚሸጠው ቆሎና ለውዝ ሲሰጠው ተመለከትኩ(የመጀመሪያው ፎቶ ላይ እንደምታዩት ማለት ነው) ከዛም የልጁ ነገር ገርሞኝ ለባልደረቦቼ ነገርኳቸውና ድጋሚ አብረው ፎቶ አነሳኋቸው (ሁለተኛው ፎቶ) ።

አስባችሁታል ይሄ ህፃን ልጅ ቆሎና ለውዝ ሽጦ የሚያገኛት ትንሽዬ ናት ነገር ግን ደስ ስላለው ለመስጠት አልሰሰተም እናም ልቡ አስቀንቶኛል ። ስንሰጥ አስልተን መስጠት እንደሌለብንም አስተምሮኛል።

ለቀና ልቡ ልጁን ደግመን ብናገኘውና የሆነች ነገር ብናደርግለትስ? አምስት ሰው ብቻ ነው የምፈልገው ፍቃደኛ የሆነ ከዛ ትንሽዬ ስጦታ እንስጠው ።

ሌሎችም እንዲማሩበት ሼር አድርጉት

Aku Image





Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: