#FastMereja I ባሮክ ኤቨንት ከተለያዩ አጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር የሰርግና ከሰርግ ጋር ግንኙነት ያላቸው ምርቶችና አገልግሎቶች በአንድ ቦታ የሚቀርቡበት በሃገራችን በአይነቱ ልዩና የመጀመሪያ የሆነ የብራዲያል ኤክስፖ በከተማችን አዲስ አበባ መሰናዳቱን ዛሬ የካቲት 27 ቀን 2017 ዓ.ም በቦናንዛ አዲስ ሆቴል በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ተገልጿል።
ኤክስፖው መጋቢት 6 እና 7/2017 ዓ.ም በቦናንዛ አዲስ ሆቴል የሚካሄድ ሲሆን በመረኃግብሩም ፋሽን ሾውና የመፀሀፍ ምረቃትን ጨምሮ ከ13 በላይ ዘርፎች ይቀርቡበታል። እንዲሁም ከ40 በላይ ሻጮች ይገኙበታል ተብሏል።
የባሮክ ሰርግ ኤክስትራቫጋንዛ 2025 የተዘጋጀው ለየት ያሉ እይታዎችን ለማሳየት፣ ተነሳሽነትን ለመፍጠር፣ ልዩ ልዩ ቅናሾችን እና በኢንዱስትሪው ውስጥ ላሉት ምርጥ እቃ አቅራቢዎችንና ሠርገኞችን ተደራሽ ለማድረግ የታሰበ ሲሆን በህይወታችን ሁሌ በጉጉት ከሚጠበቁ ሁነቶች ውስጥ የሠርግና የሙሽራ ዝግጅቶች አንዱ እንደመሆኑ መጠን፣ ይህ ታላቅ ጉዳይ ከፍተኛ የሰርግ ኢንዱስትሪ ባለሙያዎችን፣ የአልባሳት የዲኮርና የአዳራሽ ዲዛይነሮችን፣ አገልግሎት ሰጪዎችን በአንድ ጣሪያ ስር በማሰባሰብ ጥንዶች ጥንቅቅ ያለ ሰርጋቸውን እንዲያቅዱ ለማነሳሳትና ለመምራት ታስቦበት የተዘጋጀ እንደሆነ ተገልጿል።
በመረኃግብሩም ድንቅ የፋሽን ትዕይንቶች፣ ምርጥ ዲዛይነሮች የሰርግ ጋውንን፣ የሙሽራ ቀሚሶችን እና የሙሽራ ልብሶችን በማሳየት ዘመናዊና ዘመኑን የዋጁ የሙሽራ ስብስቦችን ይቀርቡበታ፣ የቀጥታ ትዕይንቶችን የኬክ ቅምሻዎችን ፣ የአበባ ዲኮር ዝግጅት ማሳያዎችን ፣የጠረጴዛና ወንበር አቀማመጥ፣ ለይአውቶችን እና የሰርግ መዝናኛ ቅድመ እይታዎችን ይቀርባሉ ተብሏል።
ይህም በአይነቱ ለመጀመሪያ ግዜ ወደር በማይገኝለት ሁኔታ ቅንጦትን ከውበት ጋር አሟልቶ የያዘ እንዲሁም እውቅ የሰርግን ጣጣ ነገር ልቅም አርገው የሚያውቁ የሠርግ እቅድ ባለሞያዎችን በተጨማሪም ለሰርግ የሚውሉ የተለያዩ ቁሳቁሶችን ያሳያል።
#ኹነት


Source: FastMereja









No comments yet.