#Ethiopia | “በዓለም ላይ በጣም ታዋቂ እና ልዩ ከሆኑ ሀገሮች አንዷ ሌሶቶ ናት። ፕሬዝዳንቱ እንዲሁም ቀሪው ዓለም ሌሴቶን መጥቶ እንዲጎበኝ በደስታ እጋብዛለሁ” ሲሉ የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሌጆኔ ምፖትጆአኔ ተናግረዋል።
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ማክሰኞ ለአሜሪካ ኮንግረስ ባደረጉት ንግግር የውጭ እርዳታ ካቋረጡባቸው ሀገራት ውስጥ “ብዙ ገንዘብ የባከነባት” ያሏትን ሌሶቶ አንስተዋል። እንደ ትራምፕ ገለጻ በሌሶቶ የ LGBTQI+* መብቶችን ለማበረታት 8 ሚሊዮን ዶላር ተመድቦ ነበር።
ድጋፉ በመቋረጡ ምክንያት በተለይም በዩናይትድ ስቴትስ ፈንድ የሚደገፉት የሀገሪቱ የጤና እና ግብርና ዘርፎች ተፅዕኖ እንደደረሳባቸው ሚኒስትሩ ተናግረዋል። ሀገሪቱ ራሷን በተሻለ መንገድ የምትችልባቸውን መንገዶች እያሳሰች እንደሆነም ነው ሚኒስትሩ ጨምረው የገለፁት።
*የኤልጂቢቲ እንቅስቃሴ ከባሕል ያፈነገጠ ጽንፈኛ ቡድን ተብሎ ሩሲያ ውስጥ ታግዷል።
#sputnik
ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ።
“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet
ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26
ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet
ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet
ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet
ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet
አማርኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et
ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://en.getutemesgen.et


Source: GetuTemesgen









No comments yet.