#Ethiopia | የአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ ከ28 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ እንደተደረገበት ተነግሯል።
የማዕከሉ ዋና ሥራ አስኪያጁ አቶ ሲሳይ ገመቹ እንደገለጹት፣ ከዚህ ውስጥ ከ22 ቢሊዮን ብር በላይ የሚሆነው በባለአክሲዮኖች የተከፈለ ካፒታል ነው።
ማዕከሉ በምስራቅ አፍሪካ ከመጀመሪያዎቹ ተርታ የሚመደብ ሲሆን፣ ሁለት ትላልቅ አዳራሾች እና ስምንት ትናንሽ አዳራሾች አሉት። በተጨማሪም በዙሪያው የሚገኙ ስድስት ህንፃዎች ወደ 1000 አልጋዎችን ወደሚይዙ ሆቴሎች እየተቀየሩ መሆኑ ተገልጿል።
ወደ 2000 ገደማ መኪኖችን ማስተናገድ የሚችል የመኪና ማቆሚያ ቦታ ያለው ይህ ማዕከል 50 የንግድ ድርጅቶችን ማስተናገድ የሚችሉ የንግድ ቦታዎችም አሉት ተብሏል።
በቀጣዮቹ ሶስትና አራት ወራት 10 ተቋማት ዝግጅቶቻቸውን ለማካሄድ ቦታ ማስያዛቸውን ዋና ስራ አስኪያጁ መናገራቸውን የዘገበው ኢፕድ ነዉ።
ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ።
“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet
ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26
ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet
ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet
ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet
ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet
አማርኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et
ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://en.getutemesgen.et
Source: GetuTemesgen









No comments yet.