የማህፀን ዉሃ መቋጠር (Ovarian CYST)መረጃው እንዲ ዳረስ ሼር ያድገትጠረ ከረጢት በማህፀን ሲኖር የማህፀን ዉሃ መቋጠር …

- Advertisement -
Sidebar AD
⚠️የማህፀን ዉሃ መቋጠር (Ovarian CYST)
መረጃው እንዲ ዳረስ ሼር ያድገት
ጠረ ከረጢት በማህፀን ሲኖር የማህፀን ዉሃ መቋጠር ወይም በህክምና አጠራሩ Ovarian CYST ይባላል፡፡
በማንኛውም እድሜ ላይ ሊከሠት የሚችል በሽታ ሲሆን በአብዛኛው ዕድሜያቸው ከ15 – 40 ያሉ ሴቶች ላይ እንደሚከሠት ጥናቶች ያሳያሉ፡፡
የማህፀን ዉሃ መቋጠር (Ovarian CYST) አይነቶች ምንምን ናቸው? 
በጣም የተለመደው ፈንክሽናል ኦቫሪያን ሲስት (Functional Ovarian Cyst) የሚባለው ሲሆን  በማህፀን እንቁላል ሲለቀቅ ቦታዉ በውሃ ሲሞላ የሚከሰት መሆኑንን ባለሙያዉ ይገልጻሉ፡፡
ሌላው ፎሊኩላር ሲስት(Follicular Cyst) የሚባለው ሲሆን÷ ይህም እንቁላል እየዳበረ ሲሄድ የተወሰነ ውሃ ይይዝና እንቁላሉ ሳይለቀቅ ሲቀር የሚፈጠር የማሕፀን ውሃ መቋጠር ነው፡፡
በጉዳዩ ላይ ሙያዊ ማብራሪያ ሊሰጡን ከጣቢያችን ጋር ቆይታ ያደረጉት  በአዲስ ህይወት አጠቃላይ ሆስፒታል የማህፀንና ፅንስ ስፔሻሊስቱ ዶክተር ትዕዛዙ አለሙ ናቸው፡፡
መንስኤው ምንድን ነው?
– ሆርሞን መዛባት ሲኖር
– indometriosis የሚባለው ችግር ካለ 
– ጠቅለል ያለ የሆርሞን መዛባት ካለ
እንዲሁም የተለያየ አይነት መንስኤ እንዳላቸው ባለሙያው ይገልፃሉ፡፡
ምልክቶቹ ምንድን ናቸው?
ህመሙ በአብዛኛዉ ምልክት አያሳይም፡፡
ምልክት የሚያሳይ ከሆነ ግን እነዚህን ነገሮች ልብ ማለት አለብን፡፡
– ከፍተኛ የሆነ ሆድ ህመም
– የሆድ እብጠት
– የወር አበባ መዛባት
– ሽንት ለመሽናት መቸገር
– ሽንት ቶሎቶሎ መምጣት
ህክምናዎቹ ምንድን ናቸው?
የቋጠረው የውሀ መጠን እና አይነት፣ የታካሚው እድሜ እንዲሁም ቋጠሮዉ የካንሰር ባህሪ አለው ወይም የለውም መለየት ህክምናዉ ከመደረጉ በፊት የሚታዩ መሰረታዊ ጉዳዮች ናቸዉ ይላሉ፡፡
በመውለጃ እድሜ ላይ ባሉ ሴቶች ላይ የሚከሰቱ አብዛኛዎቹ ovarian CYST  በክትትል ያለምንም ህክምና በራሳቸው የሚጠፉ ናቸው፡፡
ከዚህ ውጪ አልፎ አልፎ  የወሊድ መከላከያ ኪኒን ይታዘዛል፡፡ እነዚህ ኪኒኖች የተፈጠሩ መቋጠሮችን የሚጠፉ ሳይሆኑ ተጨማሪ CYST እንዳይፈጠር የሚረዱ ናቸዉ፡፡
ቀዶ ህክምና የመጨረሻ  የህክምና አማራጭ ነው የሚሉት ዶክተር ትዕዛዙ፤ የማህፀን ዉሃ መቋጠሩ(Ovarian CYST)  በአልትራሳውንድ ሲታይ መጠኑ ከ10 ሴንቲ ሜትር የሚበልጥ ከሆነ፣ ወደ ካንሰር ይሄዳል የሚል ጥርጣሬን ካሳየ እንዲሁም ከፍተኛ ህመም ካለው መሆኑን ይገልጻሉ፡፡
በዓለም ላይ ከ10 እስከ 30 በመቶ የሚሆኑ ሴቶች የማህፀን እጢ ውሃ መቋጠር ያጋጥማቸዋል።
የማህፀን ዕጢ ዉሃ መቋጠር ሶስት አይነት ሲሆን ወደ ካንሰርነት የሚቀየር ፤ ካንሰር የማይሆን እና በራሱ የሚጠፋ በሚል ይከፈላል፡፡
@seledadotio
@seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: