የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ምርቶች አቅራቢ የሆነው ቴክኖ በባርሴሎና በየዓመቱ በሚካሄደው MWC 2025 የቴክኖሎጂ አውደርእይ ላይ በመሳተፍ አዲሱን የAI ሲስተም የሚጠቀሙ የቴክኖሎጂ ምርቶቹን አስተዋውቋል።
በዚህ አመታዊ የቴክኖሎጂ ሁነት አዲሱን የTECNO AIን የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂን ከዘመናዊነት ጋር ያጣመሩ ምርቶቹን ለተጠቃሚዎች ያቀረበ ሲሆን ከነዚህም መካከል የMEGABOOK S14 የተሰኘው ላፕቶፕ አንዱ ሲሆን በዓለም እጅግ ቀላሉ እና የ14 ኢንች OLED ስክሪን ቴክኖሎጂ ያለው ነው።
የኩዋልኮም Snapdragon® X Elite ፕላትፎርም እና የTecno AI ሲስተምን በማካተት እጅግ የላቀ ፕሮሰሲንግ አቅም ያለው እንደሆነም ተገልጾዋል።
በተጨማሪም TECNO AI Glasses Pro ሌላኛው በዚህ መድረክ የተዋወቀ አዲስ ምርት ሲሆን የ50MP ካሜራ ፣ የተለያዩ ቋንቋዎችን በቀጥታ ለመተርጎም የሚያስችል አቅም፣ የMicroLED AR ዲስፕሌይ እና በAI ቴክኖሎጂ በመታገዝ ጥራት ያላቸው ምስሎችን ማንሳት የሚያስችል ዲጂታል መነፅር ነው።
ከዚህም ባለፈ የMEGABOOK T14 Air እና K15S ተከታታይ የላፕቶፖ ሞዴሎችን ያስተዋወቀ ሲሆን በAI ሲስተም በመታገዝ ለተጠቃሚዎች የዕለት ተዕለት ተግባራት ለማቅለል የሚያስችል እጅግ ቀልጣፋ ቴክኖሎጂን ይዟል። ቴክኖ ከ MediaTek ፣ Qualcomm እና Google Cloud የተሰኙ ኩባንያዎች ጋር በመተባበር የ AI ቴክኖሎጂን ለአፍሪካ ገበያ ተደራሽ ለማድረግ እየሰራ እንደሚገኝም በቴክኖሎጂ ሁነቱ ይፋ ተደርጓል።
“Stop at Nothing” በሚለው መርሁ የሚታወቀው ግዙፉ ቴክኖ የተለያዩ አዳዲስ እና ዘመናዊ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን ለአለም ገበያ በማቅረብ ይታወቃል።



Source: Yeneta Tube









No comments yet.