በሱማሊያ የአሜሪካ ኢምባሲ፣ ሞቃዲሾ ውስጥ በበርካታ አካባቢዎች የሽብር ጥቃቶች እንደታቀዱ የሚያሳዩ የታመኑ መረጃዎች እንደደረሱት የሚገልጽ ማስጠንቀቂያ ትናንት አውጥቷል።
የሽብር ጥቃት እንደሚፈጸምባቸው ከሚጠበቁት ቦታዎች አንዱ የሞቃዲሾው ዓለማቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ እንደሆነ ኢምባሲው ጠቅሷል።
ይህንኑ ማሳሰቢያ ተከትሎ፣ በአገሪቱ የሚገኙ የአሜሪካ ዲፕሎማቶች ከቦታ ቦታ እንዳይንቀሳቀሱ ታዘዋል።
ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ባለፈው ሳምንት ለይፋዊ ጉብኝት ሞቃዲሾ በደረሱበት ወቅት፣ ወደ አውሮፕላን ማረፊያው ሮኬቶች እንደተወነጨፉ ይታወሳል።
@seledadotio
@seledadotio
Related Posts
- Advertisement -








No comments yet.