የጦና ንበች ፈረሰኞችን ድል አድርገዋል !

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ሀያ አንደኛ ሳምንት መርሐግብር ዎላይታ ድቻ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 1ለ0 በሆነ ውጤት ዎላይታ ድቻ አሸንፈዋል።

የዎላይታ ድቻን የማሸነፊያ ግብ አብነት ደምሴ ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

ፈረሰኞቹ ሶስተኛ ተከታታይ ሽንፈታቸውን ሲያስተናግዱ የጦና ንቦች በበኩላቸው ተከታታይ ሶስተኛ ድላቸውን አስመዝግበዋል።

ውጤቱን ተከትሎ ዎላይታ ድቻ በ30 ነጥብ 6ኛ ደረጃ ለይ ሲቀመጥ ቅዱስ ጊዮርጊስ በአንድ አንሶ 29 ነጥብ በመያዝ 7ኛ ደረጃን ይዟል።

በሃያ ሁለተኛ ሳምንት መርሐግብር ማክሰኞ ዎላይታ ድቻ ከ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ እንዲሁም ረቡዕ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ድሬዳዋ ከተማ ይገናኛሉ።

በፍቅሩ ዘለቀ






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: