አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
ስካይ ላይት ሆቴል
የካቲት 28/2027 ዓ. ም
ይህ በዓይነቱ ልዩ እና ታሪካዊ የሆነው Grand Ethio–Africa Run በዱባይ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚከናወን ሲሆን በኢትዮጵያ እና በሌሎች የአፍሪካ አገራት እንዲሁም በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች መካከል የስፖርና ፋሽን ባህልን ትስስርን ለማጠናከር ያለመ ነው ተብሏል፡፡ ይህ ሩጫ FAS Business Group ከዱባይ ስፖርት ካውንስል ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ፣ አፍሪካ እና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶችን የዲፕሎማሲ ፣ ባህል እና ስፖርት ግንኙነቶችን በማስተሳሰር መልካም መስተጋብርን ለመፈጠር የሚያስችል ታሪካዊ ትዕይንት እንደሆነ ከአዘጋጆቸሁ ለመረዳት ተችሏል፡፡ በመጪው የፈረንጆቹ ወር ሚያዚያ 5 – 6 2025 በልዩ ልዩ ዝግጅቶች በደማቅ ሁኔታ የሚከናወን ይሆናል፡፡ ዝግጅቱ የተሳታፊ አገራትን የባህል፣ የስፖርት፣ የፋሽን እንዲሁም የማሕበራዊ አንድነትን በማጉላት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነትን ወደ ላቀ ደረጃ ከፍ ያደርጋል ሲሉ የገለፁት የዝግጅቱ አስተባባሪ ኢንጂነር ፍፁም አድነው (FIFA Match Agent) ናቸው፡፡
ዝግጅቱ ታላላቅ የስፖርት ባለሙያዎችን፣ በዘርፉ ከፍተኛ ልምድ ያላቸው እና ተፅእኖ ፈጣሪ የሆኑ ግለሰቦች እንዲሁም ለዘርፉ ልዩ ፍቅር ያላቸው ተሳታፊዎችን ያካተተ ይሆናል፡፡ በዝግጅቱ ከኢትጵያ፣አፍሪካ እና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የተውጣጡ ዲፕሎማቶች፣ ታላለቅ ሰዎች እና መሪዎችም ይገኛሉ፡፡ በተጨማሪም የባህል አጥኚዎች፣ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች፣ የማሕበራዊ ጉዳዮች ምሁራን እንዲሁም የንግድ ባሙያዎች የሚተፉበት ነው፡፡
ሚያዚያ 5 2025 የዝግጅቱ ተሳታፊዎች ምዝገባ ይካሄዳል :: የመሮጫ ቲሸርቶችም ለተሳታፊዎች ይሰራጫሉ :: በተጨማሪም ልዩ የፋሽን ትርኢት ለታዳሚዎች ይቀርባል ::
ሚያዚያ 6 ቀን 2025 ደግሞ የGrand Ethio-Africa Run በዱባይ በደማቅ ሁኔታ ይካሄዳል
በዚህ ልዩ ዝግጅት ከአፍሪካ፣ ከተባበሩት አረብ ኤምሬቶች እንዲሁም አለም አቀፍ ተሳታፊዎችን በጋራ ያጣመረ ሩጫ ይካሄዳል። ውድድሩ የስፖርት የባህል፣ ፋሽን እና የህዝብ ለህዝብ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቶችን በማጠናከር ዓለምቅፋዊ ትብብሮችን እንደሚያሰፋ ታምኖበታል፡፡
በዚህ መርሃ – ግብር የ5 እና 10ኪ.ሜ የሩጫ ውድድሮች ልምድ ያላቸው ስፖርተኞች እና ለጤናና ለመዝናናና የሚሮጡ መላው የስፖርት አፍቃሪያን የሚተፍበት ነው። በተጨማሪም የባህላዊ ዘመናዊ በዲጄ የታጀበ የዳንስ እንቅስቃሴዎች የሚታዩበት ሲሆን፣የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ እና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የባህል ጭፈራዎች የሚቀርቡበት ልዩ የመዝናናኛ ትዕይንትም ተዘጋጀቷል። መርሃ – ግበሩ የዲያስፖራውን ማህበረሰብ በኢንቨስትመንት፣ ባህል እና መዝናኛ ፕሮግራሞች በማሰባሰብ የሚቀጥል ወርሃዊ ዝግጅት እንደሆነም በመድረኩ ተጠቁሟል።
በመጨረሻም በዝግጅቱ የተሳተፉ ሁሉ የሚመሰገኑበት እና በውድደሩ አሽናፊ የሆኑት ለሽልማት የሚበቁበት የምስጋናና እውቅና መርሃ ግብር እንደሚኖር ለማወቅ ተችሏል፡፡
ዝግጅቱን በክብር ስፖንሰር ካደረጉ ድርጅቶች መካከል ራይድ ÷ ኦቪድ ÷ ዳሽን ባንክ÷ ሰዋሰው መልቲሚዲያ እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይጠቀሳሉ ::



Source: Yeneta Tube








No comments yet.